ከይር ቮክስ አፍሪካ

ከይር ቮክስ አፍሪካ

ዜና የሀገር ውስጥ

አሜሪካ ቪዛ ልዩ ጥቅም እንጂ መብት አይደለም ተባለ

Posted on 2026-03-11 12:13:30


አሜሪካ ቪዛ ልዩ ጥቅም እንጂ መብት አይደለም ተባለ

አዲስ አበባ፡— በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ የአሜሪካ ቪዛ መስጠት መብት ሳይሆን ለተወሰነ ዓላማ የሚሰጥ ልዩ ጥቅም መሆኑን ገለጹ።

አምባሳደሩ በሰጡት መግለጫ፤ አሜሪካና ኢትዮጵያ ከ120 ዓመታት በላይ በመከባበርና በትብብር ላይ የተመሠረተ የረጅም ጊዜ አጋርነት እንዳላቸው ጠቁመው፤ የቪዛ ሂደትን መገንዘብና የሚያመለክቱትን ህጎች ማክበር ለተጓዦች አስፈላጊ መሆኑን አስታወቁ።

እንደ አምባሳደሩ ገለጻ፤ ወደ አሜሪካ የሚጓዙ የውጭ አገር ዜጎች ቪዛ የተሰጣቸውን የጉዞ ዓላማ መከተል አለባቸው። ቪዛው የተሰጠበትን ዓላማ ካልከበሩ ወይም ከተፈቀደው የቆይታ ጊዜ በላይ ከቆዩ ከባድ ሕጋዊ መዘዞች ሊከሰቱ እንደሚችሉም ጠቁመዋል።

የአሜሪካ ጉምሩክና ድንበር ጥበቃ ባለሥልጣን ለውጭ አገር ዜጎች በአሜሪካ ውስጥ የሚፈቀድ የቆይታ ጊዜ እንደሚወስን ገልጸው፤ ከተፈቀደው ጊዜ በላይ መቆየት የቪዛ መሰረዝ፣ ከአገር መባረር እና በወደፊት የቪዛ ጥያቄ ላይ እገዳ ሊያመጣ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

በተጨማሪም ቪዛን በአግባቡ አለመጠቀም በወደፊት ለኢትዮጵያውያን ተጓዦች ቪዛ ማግኘትን ሊያስቸግር እንደሚችል ጠቅሰው፤ ሁሉም ተጓዦች የቆይታ ጊዜያቸውን እንዳያሳልፉ ጥሪ አቀረቡ።

እንዲሁም ወደ አሜሪካ የሚጓዙ ሰዎች ለጉዞው የሚያስፈልጉ ወጪዎችን በራሳቸው ለመሸፈን በቂ የገንዘብ አቅም እንዲኖራቸው አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመው፤ ይህም ለአሜሪካ ዜጎች የተዘጋጁ የሕዝብ ጥቅማጥቅሞችን ለመጠበቅ እንደሚረዳ  አብራርተዋል።

አምባሳደር ማሲንጋ በመጨረሻ ሕጋዊ ጉዞን ለማመቻቸት አሜሪካ ቁርጠኝነት ቢኖራትም የቪዛ ሕጎችን አለማክበር ግን ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ እንዳልሆነ አስጠንቀዋል።


አስተያየትዎን ይተው