on | 2025-10-05 02:22:35
Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin
የአቢሲንያ ባንክ ባካሄደው 29ኛ መደበኛና 16ኛ አስቸኳይ ጉባዔ የዳሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን÷ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት የባንኩ ጠቅላላ ገቢ 39 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር መድረሱን አስታውቋል።
ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ91 ነጥብ 1 በመቶ ጭማሪ ወይም 11 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ትርፍ ማስመዝገቡን አመላክቷል።
በአጠቃላይ 91 ነጥብ 4 በመቶ ጭማሪ በማሳየት 10 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ያልተጣራ ትርፍ ማግኘቱን የገለጸው ባንኩ÷ አጠቃላይ ካፒታሉም ወደ 28 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ማደጉን ገልጿል።
የባንኩ አጠቃላይ ሀብት ካለፈው ዓመት አጠቃላይ ሀብት ጋር ሲነፃፀር የ28 ነጥብ 8 በመቶ እድገት በማሳየት 286 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ደርሷልም ነው የተባለው በሪፖርቱ።
ባንኩ በዲጂታል ባንኪንግና የመረጃ ቴክኖሎጂ ግንባታ በማሳደግ 1 ሺህ 700 በላይ ኤቲኤም፣ ከ3 ሺህ 600 በላይ ፖስ እንዲሁም 49 ቨርቹዋል የባንክ አገልግሎት ማዕከል ማድረጉ ተመላክቷል።
ባንኩ ማህበራዊ ኃላፊነትን ከመወጣት አኳያ 91 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉንም ጠቁሟል።