Posted on 2026-03-11 07:14:48
አዲስ አበባ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች አዲስ ሹመቶችን መስጠታቸው ተገለጸ። ሹመቱ ከመጋቢት 2 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ተፈጻሚ እንደሚሆን ታውቋል።
በሹመቱ መሠረት ሌተና ጄኔራል አስራት ደኔሮ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾመዋል። በተመሳሳይ ረዳት ኮሚሽነር ቶፊቅ መደድ የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል።
በተጨማሪም አቶ ኤርዚቅ ኢሳ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሆነው መሾማቸው ተገልጿል።
አዲሱ ሹመት በዋናነት በከተማዋ የፀጥታ አገልግሎትን ለማጠናከር፣ የህግ አስከባሪ ተቋማትን አቅም ለማሳደግና ለነዋሪዎች የተሻለ የፀጥታ አገልግሎት ለማቅረብ ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።
ከተማዋ በፍጥነት እየተስፋፋች ባለችበት ሁኔታ የፀጥታ ተቋማትን ውጤታማነት ማጠናከር እና የህዝብ ደህንነትን ማረጋገጥ በከተማዋ የሚፈልገው ዋና ጉዳይ መሆኑ ተጠቁሟል።
አዲሱ አመራር የኮሚሽኑን ሥራ በተጠናከረ መልኩ በመምራት በከተማዋ የህግ አክባሪነትን ለማሻሻልና የፀጥታ ሁኔታን ለማጠናከር ይሰራል ተብሏል።