on | 2025-12-19 12:11:16
Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin
የዩናይትድ ስቴትስ ብራውን ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ከተፈጸመው የተኩስ እሩምታ እና ግድያ በኋላ የ«ዲቪ» ሎተሪ እድልን ማገዷን ዐሳወቀች ። የዩናይትድ ስቴትስ የአገር ውስጥ ደኅንነት መሥሪያ ቤት ኃላፊ ክሪስቲ ኖዬም፦ በብራውን ዩኒቨርሲቲ የተኩስ እሩምታ ግድያ የተጠረጠረው ግለሰብ «አሁን በተቋረጠው የዲቪ መርኀ-ግብር ተጠቃሚ ከሆነ አገር የመጣ ነው» ብለዋል ። ለኃላፊዋ የዲቪ ሎተሪ እድል መርኀግብሩን እንዲያቋርጡ «አቋርጪ» ሲሉ ትናንት ሐሙስ፤ ታኅሣሥ 9 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ማምሻውን ትእዛዝ ያስተላለፉላት የአገሪቱ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ናቸው ።
«በፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ መመሪያ መሠረት ከእንግዲህ በዚህ አደገኛ መርኀ-ግብር አንድም አሜሪካዊ እንደማይጎዳ እርግጠኛ እስክንሆን ድረስ የዲቪ ሎተሪን መርኀ-ግብር እንዲያቋርጥ ለዩናይትድ ስቴትስ ዜግነት እና ኢሚግሬሽን አገልግሎት ወዲያውኑ አስተላልፌያለሁ» ሲሉ ክሪስቲ ናዮም ዐሳውቀዋል ። ኃላፊዋ በይፋዊ የኤክስ ማኅበራዊ መገናኛ አውታራቸው እንደጻፉትም በብራውን ዩኒቨርሲቲ የተኩስ እሩምታ ገዳዩ ክላውዲዮ ማኑዌል ኔቬስ ቫሌንቴ፦ «እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር በ2017 የዲቪ ሎተሪ መርኀ ግብር ግሪን ካርድ አግኝቶ» ዩናይትድ ስቴትስ የገባ ነው ።
የዲቪ ሎተሪ መርኀ-ግብር በየዓመቱ 50,000 ፍልሰተኞች ወደ ዩናይትድ ስቴትስ እንዲገቡ የሚያስችል እድል እንደነበር ነው የተገለጸው ። በዚህ እድል በርካታ ኢትዮጵያውያንም ተጠቃሚዎች ናቸው ።
የዲቪ እድል መርኀ-ግብር እንዲቋረጥ በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በተላለፈው ውሳኔ ላይ አስተያየታችን አጋሩን፤ ተወያዩበት ።
ዘገባው የDW ነው
በወላይታ ብሔር ዘንድ ልዩ ቦታ የሚሰጠው "ጊፋታ”
በቶኪዮ የወርቅ መርገም አልሰበር ያላት ኢትዮጲያ