ከይር ቮክስ አፍሪካ

ከይር ቮክስ አፍሪካ

ዜና የሀገር ውስጥ

በመንግስት ቢሮዎች ውስጥ እየገባ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ሲሰርቅ የነበረ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ

on | 2026-03-05 10:20:46

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin


በመንግስት ቢሮዎች ውስጥ እየገባ  ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ሲሰርቅ የነበረ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ፡– በከተማዋ ውስጥ በተለያዩ ቢሮዎች በመግባት ላፕቶፖችን፣ ታብሌቶችንና የሞባይል ስልኮችን ሲሰርቅ የነበረ አንድ ግለሰብ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በተደረገ ትብብር ከተደበቀበት ቦታ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ።

ፖሊስ እንደገለጸው፤ ቢንያም ሱራፌል የተባለው ተጠርጣሪ በከተማዋ የተለያዩ ቢሮዎች ውስጥ በመግባት ልዩ ልዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ሲሰርቅ ከቆየ በኋላ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 በሚገኘው አርሴማ ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ከተከራየው መኖሪያ ቤት ተይዟል።

ተጠርጣሪው በቢሮዎች ውስጥ እየገባ የሚፈጽመውን የስርቆት ድርጊት የሚያሳዩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች በዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ (Citizen Engagement Application) እና EFPApp እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያዎች በተሰጡ ጥቆማዎች ለፖሊስ መድረሳቸውን መምሪያው ገልጿል።

ከዚህ ቀደም ተጠርጣሪው ተይዟል ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨ መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን ፖሊስ ጠቁሞ፤ ይህም ተጠርጣሪውን ለመያዝ እንዲያዳክም ቢያደርግም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ ክትትል ከተደረገ በኋላ ዛሬ የካቲት 23 ቀን 2018 ዓ.ም በቁጥጥር ስር ሊውል እንደቻለ ገልጿል።

ፖሊስ በተጨማሪም ተጠርጣሪው ከዚህ ቀደም ወንጀል ፈጽሞ የተጎዱ ግለሰቦች ካሉ በአካል በመገኘት መረጃ እንዲሰጡ ጥሪ አቅርቧል። በተመሳሳይ ህብረተሰቡ ያልተረጋገጠ መረጃ ከማጋራት እንዲቆጠብ እና ከፖሊስ የሚወጡ መረጃዎችን ብቻ እንዲከታተል አሳስቧል።


አስተያየትዎን ይተው