ከይር ቮክስ አፍሪካ

ከይር ቮክስ አፍሪካ

ዜና አለም አቀፍ

አል.ሲሲ እና ትራምፕ ያቀዱት ድርድር ምን መልክ ይዞ ይመጥ ይሆን?

on | 2026-01-21 19:07:55

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin


አል.ሲሲ እና ትራምፕ ያቀዱት ድርድር ምን መልክ ይዞ ይመጥ ይሆን?

አዲስ አበባ - የግብፅ ፕሬዝዳንት አብደልፈታህ አል-ሲሲ ዛሬ በዋሽንግተን ዲሲ ከአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ተገናኙ። ውይይቱ  የናይል ውሃ ጉዳዮችን፣ የደህንነት ትብብርን ጨምሮ በሰፊው የተመለከተ ነበር ተብሏል።

ይህ ስብሰባ በኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ እና የውጭ ጉዳይ ተንታኞች መካከል አዲስ ውይይት እየፈጠረ ሲሆን፣ በዚህ አውድ ውስጥ የተናገረው ፖለቲከኛ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ናቸው።

ደሳለኝ በፌስቡክ ገጹ ላይ ባሰፈረው አስተያየት፣ ግብፅ በግድቡ (GERD) እና በናይል ውሃ ጉዳይ አስመልክታ በኢትዮጵያ ላይ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ እና የጂኦፖለቲካ ግፊት እያደረገች መሆኑን ገልጿል።

“በቀጣዮቹ ወራት ስለታቀዱት ድርድሮች ግልጽነት እየጠበቅን ቢሆንም፣ በመሬት ላይ ያለው እውነታ ግልጽ ነው፤ ግብፅ በኢትዮጵያ ላይ ሙሉ የዲፕሎማሲና የጂኦፖለቲካ ጡንቻዋን እያጠናከረች ነው” ሲሉ ፅፈዋል።

ደሳለኝ አክሎም “መንግስት/የውጪ ጉዳይ ሚ/ር በዚህ ጉዳይ ላይ ‘ቄሱም ዝም መጽሐፉም ዝም’ ማለቱ በኢትዮጵያ ዘመናዊ የውጭ ግንኙነት ታሪክ ውስጥ ያልተለመደ ነው” ሲሉም ገልፀውል።

እንዲሁም የኢትዮጵያ አስቸጋሪ የዲፕሎማሲ ዘመን ወደፊት እየቀረበ ቢሆንም፣ ለህዝቡ ስለ ተደረገ ወይም ስለሚደረግ ሀገራዊ ዝግጅት ግልጽ መረጃ እንዳልተሰጠ ዶ/ር ድሳለኝ ገልፀዋል።

“አስቸጋሪ ጊዜ ከፊታችን እየመጣ ሲሆን፣ ለዚህ ሁኔታ የሚመጥን ሀገራዊ ዝግጅት እየተደረገ ስለመሆኑ ለኢትዮጵያ ህዝብ የተሰጠ ምንም መረጃ የለም” ብለዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት በግድቡ ጉዳይ ላይ የሚከተለው አቋም የልማት መብትን እና የሀገራት  ትብብርን የሚያጎላ ሲሆን፣ ከዛሬው የሲሲ–ትራምፕ ቀጠሮ በኋላ ግን ከመንግስት በኩል ይህንን ጉዳይ በተመለከተ አዲስ መግለጫ እስካሁን አልወጣም።

ፈልግ

አስተያየትዎን ይተው