on | 2026-01-19 12:59:17 on2026-01-19 14:39:11
Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin
አዲስ አበባ፦ የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ ዛሬ በአዲስ አበባ ጃንሜዳ በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ-ሥርዓት እየተከበረ ይገኛል።
በበዓሉ ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ፣ የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ እና ሌሎች ተገኝተዋል ።
በተጨማሪም በጃንሜዳው እየተከበረ ባለው በዓል ላይ በርካታ ፣ ምዕመናን፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎችና የውጭ ሀገራት ጎብኚዎች ተገኝተዋል።
ሌሎች ከፍተኛ የቤተክርስቲያኗ አባቶችም በበዓሉ ላይ በመገኘት ጸሎት ትምህርተ ወንጌል እያስተላለፉ ይገኛሉ።
የሊቃውንቱ ያሬዳዊ ወረብና ሽብሸባ እንዲሁም የምዕመናኑ መንፈሳዊ ዝማሬ ለበዓሉ ልዩ ድባብ ሰጥቶታል።
የጥምቀት በዓል በዩኔስኮ በማይዳሰሱ የዓለም ቅርሶች ዝርዝር ውስጥ መመዝገቡ የሚታወስ ሲሆን፣ በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባና በመላው ኢትዮጵያ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
በወላይታ ብሔር ዘንድ ልዩ ቦታ የሚሰጠው "ጊፋታ”
በቶኪዮ የወርቅ መርገም አልሰበር ያላት ኢትዮጲያ