on | 2025-10-17 12:05:23
Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin
* ኮለኔሉ ቃላ መሐላ ሊፈፅሙ ነዉ
የአፍሪቃ ሕብረት ማዳጋስካር ዉስጥ ተደረገ ያለዉን መፈንቅለ መንግሥት አወገዘ።ሕብረቱ ትናንት
ባወጣዉ መግለጫ የማዳጋስካር ጦር ኃይል የሐገሪቱን የመንግሥትነት ሥልጣን መያዙን ተቃዉሟል።ሕብረቱ ከዚሕ ቀደም ወታደራዊ መፈንቅለ-መንግሥት
በሚደረግባቸዉ አባል ሐገራት ላይ እንደሚያደርገዉ ሁሉ ማዳጋሥካርን ለጊዜዉ ከአባልነት አግዷልም።
በሐገሪቱ ባስቸኳይ ምርጫ እንዲደረግና የሲቪል አስተዳደር እንዲመለስ ሕብረቱ አሳስቧልም።አዲሱ የማዳጋስካር ወታደራዊ
መሪ ኮሎኔል ማይክል ራንድርያኒሪና ነገ አርብ ቃለ መሐላ ፈፅመዉ የመሪነቱን ሥልጣን በይፋ እንደሚይዙ አረጋግጠዋል።የማዳጋስካር
ጦር-ኃይል የአስተዳደርና የቴክኒክ አገልግሎት ጓድ (CAPSAT) አዛዥ ኮሎኔል ራንድርያኒሪና የፕሬዝደንት አንድሬይ ራጆሊናን አስተዳደር
ይቃወሙ ነበር። የ51 ዓመቱ ኮሎኔልና የሚያዙት ጦር ባልደረቦች የማዳጋስካር ወጣቶች የራጆሊናን አስተዳደር በመቃወም በተከታታይ
የሚያደርጉትን ሠልፍ በግልፅ የተቀየጡት ባለፈዉ ቅዳሜ ነበር።
ወጣቶቹ የፕሬዝደንት ራጆሊናን አስተደደር የተቃወሙት የኑሮ ዉድነት፣ሥራ አጥነት፣ የኤሌክትሪክ
ኃይል መቆራረጥ ሥላስመረራቸዉ ነዉ። የፀጥታ ኃይላት ተቃዉሞዉን ለማዳፈን በወሰዱት የኃይል እርምጃ ከ20 በላይ ሰዎች ተገድለዋል።አመፁ
በማየሉ ከሐገር የሸሹት ወይም የተሰወሩት ፕሬዝደንት ራጆሊና ጦር ኃይሉ ሥልጣን መያዙne ተቃዉመዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ተከታታይ የተቃውሞ ሰልፍ ከተካሄደባቸው በኋላ የሸሹት የማዳጋስካር ፕሬዝዳንት አንድሬ ራጆሊና ከሀገራቸው መሰደዳቸውን አረጋገጡ። «ርዕሰ ብሔሩ በሕይወታቸው ላይ ግልጽ እና እጅግ በጣም ከባድ ዛቻዎች» እንደተሰነዘሩባቸው የጠቀሰው የፕሬዝዳንቱ ጽህፈት ቤት ትናንት ማምሻውን ያወጣው መግለጫ ራጆሊና በሰኞና በማክሰኞ መካከል ከሀገር መውጣታቸውን አስታውቋል። ዘገባዎች እንደሚሉት የ51 ዓመቱ ራጆሊና ባለፈው እሁድ ነበር በፈረንሳይ ወታደራዊ አውሮፕላን ከሀገር የወጡት። ከዚያ በኋላ ሰኞ ባወጡት መግለጫ ደኅንነቱ በተጠበቀ ስፍራ እገኛለሁ ከማለት ውጭ በትክክል የት እንዳሉ አልገለጹም።
በወላይታ ብሔር ዘንድ ልዩ ቦታ የሚሰጠው "ጊፋታ”
በቶኪዮ የወርቅ መርገም አልሰበር ያላት ኢትዮጲያ