ከይር ቮክስ አፍሪካ

ከይር ቮክስ አፍሪካ

ዜና የሀገር ውስጥ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ በረራዎችን ለጊዜው አቋረጠ

on | 2026-02-28 20:13:34 on2026-03-01 14:09:27

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ በረራዎችን ለጊዜው አቋረጠ

አዲስ አበባ - የኢትዮጵያ አየር መንገድ (Ethiopian Airlines) በመካከለኛው ምሥራቅ እየተከሰተ ባለው የጸጥታ ችግኝ ምክንያት ወደ አካባቢው እና ከአካባቢው ወደ አዲስ አበባ የሚደረጉ በረራዎችን ለጊዜው መሰረዙን አስታወቀ።

አየር መንገዱ ወደ ቤሩት፣ ቴላቪቭ፣ ኦማን እና ዳማም እንዲሁም ከእነዚህ መነሻዎች ወደ አዲስ አበባ የሚደረጉ በረራዎች ላይ ጊዜያዊ እገዳ መጣሉን ገልጿል።

የአየር መንገዱ ውሳኔ ዋና አላማ  የተጓዦችን እና የአብራሪዎችን ደህንነት መጠበቅ መሆኑን አስታውቆ፣ በቀጠናው ያለውን ሁኔታ በቅርብ እየተከታተለ መሆኑን ገልጧል። 

ሁኔታው እንደሚሻሻል በመጠባበቅ ተጨማሪ ርምጃዎች እንደሚወስድ የጠቀሰ ሲሆን፣ በረራዎቹ መቼ እንደሚጀምሩ በቀጣይ እንደሚገለጽ አሳውቋል።

ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ወይም ከዚያ ወደ አዲስ አበባ መጓዝ ያቀዱ ደንበኞች የበረራ መረጃዎቻቸውን በድርጅቱ ድረ-ገፅ እና በሌሎች ዲጂታል የመረጃ ምንጮች እንዲከታተሉ ጠይቀዋል።

 አየር መንገዱ የተጓዦች ጥያቄዎችን ለመመለስ የደንበኛ አገልግሎት ማዕከሉ ዝግጁ መሆኑንም ገልጿል።


አስተያየትዎን ይተው