ከይር ቮክስ አፍሪካ

ዜና የሀገር ውስጥ

ጃፓን እና የአለም ጤና ድርጅት በትግራይ ለሚገኙ ሶስት ሆስፒታሎች አምቡላንስ እና የህክምና መሳሪያዎች ድጋፍ አደረጉ

on | 2025-10-17 11:27:49 on2025-12-01 01:37:52

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin


ጃፓን እና የአለም ጤና ድርጅት በትግራይ ለሚገኙ ሶስት ሆስፒታሎች አምቡላንስ እና የህክምና መሳሪያዎች ድጋፍ አደረጉ

የጃፓን መንግስት እና የአለም ጤና ድርጅት ያደረጉት ድጋፍ በትግራይ ክልል ለሚገኙት ለአዲዳዕሮ የመጀመሪያ ሆስፒታል፣ ለፍሬወይኒ የመጀመሪያ ሆስፒታል እና ለዕዳጋ ዓርቢ የመጀመሪያ ሆስፒታሎችን ለመደገፍ እና በሰሜን ኢትዮጵያ የአደጋ ጊዜ ዝግጁነትን ማሳደግ ላይ ያተኮረ ነው።

በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ እንደተናገሩት የአለም ጤና ድርጅት ቀጣይነት ያለው ድጋፍ የኢትዮጵያን የጤና ስርዓት ለማጠናከር ትልቅ ፋይዳ አለው። የጃፓን ህዝብና መንግስት ላደረጉት ትብብርና ወቅታዊ አስተዋፅኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ድጋፉ ሆስፒታሎቹን በማደስ ሙሉ አገልግሎት መስጠት እንደሚስችላቸው ዶ/ር ደረጀ ተናግረዋል። 

በኢትዮጵያ የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ ፕ/ር ፍራንሲስ ቺሳካ ካሶሎ ድጋፉ የጤና ተቋማትን እድሳት፣ መልሶ ማቋቋም እንዲሁም የውሃ እና የንፅህና አጠባበቅ ስርዓትን ወደ ነበሩበት መመለስንም የሚያካትት መሆኑን አብራርተዋል። በሦስቱ ሆስፒታሎች የሚገኙ የእናቶችና ድንገተኛ ህክምና ክፍሎች አቅማቸውን ለማሳደግ ከፍተኛ ማሻሻያ እንደሚደረግላቸው ጨምረው ገልፀዋል።

በጃፓን ኤምባሲ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ ሚስተር ኔትሱ ሹንታሮ እንዳሉት ድጋፉ በትግራይ፣ አማራ እና አፋር ክልሎች የሚኖሩ ከ150,000 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች አስፈላጊ የሆነውን የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ያስችላል። ሁሉም ዜጎች በችግር ጊዜም ቢሆን ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ ኢትዮጵያ የጤና ስርዓቷን በመገንባትና በማጠናከር የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ ጃፓን ቁርጠኛ መሆኗንም አረጋግጠዋል።

የአምቡላንስ እና የህክምና ማሳሪያዎች ድጋፉን የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር አማኑኤል ሃይሌ ተረክበዋል።

ፈልግ

አስተያየትዎን ይተው