ከይር ቮክስ አፍሪካ

ዜና የሀገር ውስጥ

ከ956 ሺህ በላይ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎቶች በኦንላይን ተሰጡ

on | 2025-10-17 11:05:28

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin


ከ956 ሺህ በላይ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎቶች በኦንላይን ተሰጡ

በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ956 ሺህ በላይ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎቶች በኦን ላይን መሰጠታቸውን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሴክተር መስሪያ ቤቶች የሩብ ዓመት  አፈጻጸም ገምግሟል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በወቅቱ እንደገለጹት፤ 956 ሺህ 858 የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎቶች በኦን  ላይን ተሰጥተዋል፡፡

የሩብ ዓመቱ አፈጻፀም ከእቅዱ የ41 በጥብ 5 በመቶ ብልጫ አለው ብለዋል።

የተገኘው ውጤት በበጀት ዓመቱ ማጠናቀቂያ የታቀደውን ሶስት ሚሊዮን የኦንላይን አገልግሎት ማሳካት እንደሚቻል ያሳየ  መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ምንጭ፡- ጋዜጣ_ፕላስ 

ፈልግ

አስተያየትዎን ይተው