ከይር ቮክስ አፍሪካ

ዜና የሀገር ውስጥ

ብሔራዊ ባንክ ያካሄደው የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ውጤት ይፋ ሆነ

on | 2025-10-14 13:15:28

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin


ብሔራዊ ባንክ ያካሄደው የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ውጤት ይፋ ሆነ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ያካሄደው የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ውጤት ይፋ ሆኗል።
በጨረታ ሒደቱ 31 ባንኮች የተሳተፉ ሲሆን÷ በዚህም የምንዛሪ ጨረታ አንድ የአሜሪካን ዶላር ዋጋ በአማካኝ 148 ነጥብ 1007 ብር ሆኖ መመዝገቡ ተገልጿል፡፡
ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ገበያን በመገምገም በቀጣይም ተመሳሳይ የውጭ ምንዛሪ ጨረታውን እንደሚቀጥል አመላክቷል፡፡
ከውጭ ምንዛሪ ገቢ ከፊሉን ለባንኮች በጨረታ ማቅረቡ በባንኮች ዘንድ የሚኖረውን የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት በመደገፍ የዋጋ እና የውጭ ምንዛሪ መረጋጋት እንዲፈጠር ማስቻሉን ባንኩ ጨረታውን አስመልክቶ ባወጣው መረጃ ገልጿል።
ብሔራዊ ባንክ በትናንትናው ዕለት 150 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ለውጭ ምንዛሪ ጨረታ ማዘጋጀቱን መግለጹ ይታወሳል።

ፈልግ

አስተያየትዎን ይተው