ከይር ቮክስ አፍሪካ

ዜና የሀገር ውስጥ

ባንኩ ሶስት ነጥብ 85 ቢሊዮን ብር ትርፍ አስመዘገበ

on | 2025-10-07 12:43:18

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin


ባንኩ ሶስት ነጥብ 85 ቢሊዮን ብር ትርፍ አስመዘገበ

በተጠናቀቀዉ የ2017 በጀት ዓመት የሶስት ነጥብ 85 ቢሊዮን ብር  ትርፍ ማስመዝገቡን ወጋገን ባንክ አስታወቀ።

ወጋገን ባንክ አክስዮን ማህበር 32ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤዉን እያካሄደ ይገኛል።

የተጠናቀቀዉን የ2017 በጀት ዓመት የባንኩን የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት የወጋገን ባንክ የዳይሬክቶሬት ቦርድ ሰብሳቢ አብዲሹ ሁሴን እንደተናገሩት፤ ባንኩ በበጀት ዓመቱ እንደ ሀገር የተወሰኑ  ሪፎርሞች መልካም አጋጣጣሚዎችን በመጠቀም ዉጤታማ የሚባሉ ስራዎችን አከናዉኗል ።

በበጀት ዓመቱም በባንኩ የስራ እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ የፈጠሩ ችግሮች የነበሩ ቢሆንም፤ ይህንን በማለፍ ከታክስ በኋላ ሁለት ነጥብ 78 ቢሊዮን ብር ማስመዝገቡ ገልጸዋል።

የባንኩ የተቀማጭ ሂሳብ ደንበኞች ቁጥርም ከአራት ሚሊዮን 376 ሺህ በላይ መድረሱንና የተቀማጭ ገንዘብ መጠን 66 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር መድረሱን ተናግረዋል።

ምንጭ:- ጋዜጣ_ፕላስ |

ፈልግ

አስተያየትዎን ይተው