on | 2025-12-05 12:41:04
Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin
አዲስ አበባ - በቀድሞው የሠላም ሚኒስትር ዴኤታ እና የኦሮሚያ ምክር ቤት አባል የነበሩት ታዬ ደንደአ ጥፋተኛ በተባሉበት ክስ የ7 ዓመት ከ2 ወር እስር ተፈረደ።
ታዬ ዛሬ አርብ ኅዳር 26/2018 ዓ.ም. የቅጣት ውሳኔ የተላለፈባቸው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሕገ መንግሥት እና በሕገ መንግሥት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ችሎት ጥፋተኛ በተባሉበት ሕገወጥ የጦር መሣሪያ ይዞ በመገኘት ነው።
የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣን እና የክልል ምክር ቤት አባል የነበሩት ታዬ ሕገ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ይዞ በመገኘት እንዲሁም ፍቃድ ሳይኖራቸው በቤታቸው ውስጥ አንድ ታጣፊ ክላሽንኮቭ ጠመንጃ ከ60 ጥይቶች ጋር ተገኝቷል በሚል ክስ ቀርቦባቸው ነበር።
በወላይታ ብሔር ዘንድ ልዩ ቦታ የሚሰጠው "ጊፋታ”
በቶኪዮ የወርቅ መርገም አልሰበር ያላት ኢትዮጲያ