on | 2025-12-01 12:45:22 on2025-12-01 13:23:33
Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin
አዲስ አበባ፡- በዛሬው ዕለት የጂኦ-ፖለቲካ ተመራማሪ የሆኑት ዕጩ ዶ/ር ትዕግስቱ አወሉ ከከይር ቮክስ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ ኢትዮጵያ በባህር በር ላይ ያላት ፍላጎት ከታሪካዊ ይዞታዋ የመነጨ ነው ሲሉ ገልፀዋል።
ኢትዮጵያ በታሪክ ምህዳሯ ከቀይ ባህር ጋር ያለት ግንኙነት ከዘመናት በፊት የቆየ ነው። የዛሬው የባህር በር ምኞትም ስንመለከተው ታሪካዊ ዳራዉን የተከተለ ጥያቄ ነው።
ታሪካዊ ምህዳሩም ከቅድመ አክሱም ስልጣኔ በፊት ጎልቶ ከሚታየው ከዳማት ስልጣኔ መንግስት ሲሆን በተለይም በ3ኛው ክፍለ ዘመን በአክሱም ዘመነ መንግስት ሰፊ ንግድ እና ግብይት ከተካሄዱት አበይት ክንውኖች መካከል ከቀይ ባህር ማዶ ካሉ ሀገራት ማለትም ህንድ፣ ሳውዲ አረቢያ እና የመን ጋር እንደ ቅመማ ቅመም ያሉ ሸቀጦችን ስትለዋወጥበት የነበረ የንግድ መስመር እንደነበርም አብራርተዋል።
ተመራማሪው እንዳሉት፤ ከ3ኛው-7ኛው ክፍለ ዘመንም የቀይ ባህር ቁጥጥር በሀገራችን በአክሱም ስልጣኔ ዘመነ መንግስት ስር የነበረ ቢሆንም ከስልጣኔ መንግሥቱ መውደቅ ጋር ተያይዞ ሌሎች የስልጣኔ መንግሥታት ሲነግሱ ስታስተዳድራቸው የነበሩ ወደቦቿን ቀስ በቀስ አጣቸዋለች ሲሉ ተናግረዋል።
ተመራማሪው በአሁኑ ጊዜ ታሪኩን ከማስጠበቅ ባለፈ የይገባኛል ጥያቄ መነሳቱ በዘመናችን ካለዉ የጂኦ-ፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ጉዳዮች አንፃር ትክክል ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ባላት የህዝብ ብዛቷ 2ኛ ደረጃ የያዘች ሲሆን በአፍሪካ ቀንድ ውሰጥ ከሚገኙ ሀገራት መካከልም አንዷ ነች። በውስጧም 3 ዋና ዋና የሚባሉ እንደ ቀይ ባህር፣ የኤደን ሰላጤ እና ባልባብ ወደቦች ነዳጅን ጨምሮ የትልልቅ መርከቦች መተላለፊያ ሀገር ከመሆኗ አንፃር በታሪካዊ መንገድም ወደብ የማግኘት መብት አላት ሲሉም ገልፀዋል።
የጂኦግራፊ አቀማመጧም ካሉት በአፍሪካ ቀንድ ወደቦች ካሏቸው ሀገራት ጂቡቲ፣ ሱዳን እና ኤርትራ በአቅራቢ የምትገኝ ሀገር እንደመሆኗ፤ በኢኮኖሚውም ቢሆን ለወደብ ኪራይ በዓመት ወደ 2 ቢሊየን ዶላር ገደማ ታወጣለች።
ወደብ ላከራየቻት ጎረቤት ሀገር ጂቡቲ በዓመት ከወደብ ኪራዮቿ የምታገኘውን 50 በመቶ ያህሉን የምታገኘው ከኢትዮጵያ ነው ሲሉ ጠቅሰዋል።
በፖለቲካ ጉዳይም አስተያየታቸውን የሰጡት የጂኦ ፖለቲካ ተመራማሪው ዕጩ ዶ/ር ትዕግስቱ አወሉ ሀገሪቱ የራሷ የወደብ መዳረሻ ስለሌላት ደህንነቷንም የሚነካ አሳሳቢ ጉዳይ እንደሆነም ገልፀው የኢትዮጵያ የባህር በር ፍላጎት ከታሪካዊ ይዞታ የመነጨ ነው! ብለዋል።
ሮዛ ነዚፍ
ሙሉውን ቃለ ምልልስ በይትዩብ ቻናላችንን ይከታታሉ
በወላይታ ብሔር ዘንድ ልዩ ቦታ የሚሰጠው "ጊፋታ”
በቶኪዮ የወርቅ መርገም አልሰበር ያላት ኢትዮጲያ