የተቋማት ሪፎርም ወይም የማሻሻያ ስራ እየተደረገባቸው ካሉት መካከል የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አንዱ ነው፡፡ 

በዚሁ ማሻሻያ መሰረት የመንግስት ሰራተኛው ብቁ እንዲሆን ባህሪውንና የተሰማራበትን የስራ ዘርፍ የሚመዝን ፈተና ይሰጠዋል ተብሏል፡፡

ፈተናውን የወደቀና ስልጠናም ወስዶ ተመሳሳይ ውጤት ያመጣ ከስራው እንደሚባረርም ኮሚሽኑ ተናግሯል፡፡

የምዘናው ዋና ዓላማ ግን ሰዎችን ከስራ ማባረር ሳይሆን ብቁ ሰራተኛ ለመፍጠር ያለመ ነው ይላል ኮሚሽኑ፡፡