on | 2025-11-18 18:10:33 on2025-12-01 00:20:20
Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin
አዲስ አበባ:- የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ ምክር ቤቱ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ከሙስሊሙ መሪ ተቋም ጋር ሳይወያይ፣ ሙስሊም ተማሪዎች በግዳጅ ግዕዝ ቋንቋ እንዲማሩ ውሳኔ ማሳለፉ በፍጹም ተቀባይነት የለውም ሲል ዛሬ ባወጣው መግለጫ አቋሙን ገልጧል።
ምክር ቤቱ፣ የክልሉ ትምህርት ቢሮ በውሳኔው ላይ የእርምት እርምጃ እንዲወስድ ጠይቋል።
የትምህርት ቢሮው ውሳኔ የሙስሊሙን ማኅበረሰብ እና የሙስሊሙን ተቋማት ባገለለ መልኩ የተተላለፈ ነው ያለው ምክር ቤቱ፣ ውሳኔው ክልሉ የገጠሙትን ውስብስብ ችግሮች ይበለጥ ያወሳስባል በማለት አስጠንቅቋል።
ምክር ቤቱ፣ በትግራይ ክልል የሚገኙ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ሙስሊም ተማሪዎችን በኢስላማዊ አለባበሳቸው ምክንያት ከሁለት ዓመታት በላይ ከትምህርት ገበታ ሲያግዱ፣ ትምህርት ሚንስቴር ተማሪዎቹ ወደ ትምህርታቸው እንዲመለሱ ምንም ዓይነት ጥረት አላደረገም በማለትም ወቅሷል።
ኢስላማዊ አልባሳትን ለብሶ መማር ሕገመንግስታዊና ኃይማኖታዊ መብት መሆኑን ምክር ቤቱ በመግለጽም፣ ትምህርት ሚንስቴርና አንዳንድ የትምህርት ተቋማት ሙስሊሞችን በኢስላማዊ አለባበሳቸው ሳቢያ ከትምህርት የማፈናቀል ድርጊቶችን ባስቸኳይ ሊያቆሙ ይገባል ብሏል።
ለእነዚህ ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ የሚያፈላልግ ኮሚቴ ማቃቋሙንም ምክር ቤቱ አስታውቋል።
በወላይታ ብሔር ዘንድ ልዩ ቦታ የሚሰጠው "ጊፋታ”
በቶኪዮ የወርቅ መርገም አልሰበር ያላት ኢትዮጲያ