ከይር ቮክስ አፍሪካ

ዜና የሀገር ውስጥ

ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የ3ኛ ዓመት ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስገድደው መመሪያ በ2019 የትምህርት ዘመን ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።

on | 2025-11-18 13:17:17

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin


ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የ3ኛ ዓመት ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ            ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስገድደው  መመሪያ በ2019 የትምህርት ዘመን ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።

ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የ3ኛ ዓመት ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ 

          ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስገድደው 

          መመሪያ በ2019 የትምህርት ዘመን ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።

 ለመምህራን የሚቀርበው ጥቅማጥቅምና ደመወዝ በቂ አለመሆን 

           ለመምህራን እጥረት ምክንያት እንደሆነ የትምህርት ሚኒስትሩ  

          ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ለምክር ቤት አባላት ተናግረዋል። ይህም አዲስ 

           መምህራንን በበቂ ሁኔታ ለማፍራት አስቸጋሪ እንዳረገው 

           ገልፀዋል።

የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ግለሰቦች የአንድ ዓመት የማስተማር 

           ዘዴ (Pedagogy) ኮርስ በመውሰድ ለመምህርነት ብቁ መሆን 

           እንደሚችሉ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል። በዚህም የመምህራንን ቁጥር 

           ለማሳደግ ይቻላል ብለዋል። 

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት 

          ሲሰጡ፣ የበለጠ የመምህነነት ሙያ ፍቅር ሊያጎለብቱ 

          እንደሚችሉም ገልፀዋል። 

ባለፈው ዓመት ከቅድመ-አንደኛ እስከ 12ኛ ክፍል በሀገሪቱ 

          አጠቃላይ የመምህራን ቁጥር 625,000 የነበረ ሲሆን፤ በዚህ ዓመት 

         ቁጥሩን ወደ 700,000 ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል።

ፈልግ

አስተያየትዎን ይተው