ከይር ቮክስ አፍሪካ

ዜና የሀገር ውስጥ

እንጀራ እና ዳቦ በሸቀጣ ሸቀጦች ሱቅ መሸጥ ተከለከለ

on | 2025-11-17 18:38:02 on2025-12-01 00:19:40

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin


እንጀራ እና ዳቦ በሸቀጣ ሸቀጦች ሱቅ መሸጥ ተከለከለ

አዲስ አበባ:- እንጀራ እና ዳቦ በሸቀጣ ሸቀጦች ሱቅ መሸጥ መከልከሉ ተገለጸ። የአዲስ አበባ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣንን የተለያዩ ሸቀጣሸቀጦች በሚሸጡባቸው ሱቆች ውስጥ እንጀራ እና ዳቦ መሸጥ መከልከሉን አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዘግቧል:: 

ባለስልጣን መ/ቤቱ የተለያዩ መርዛማ ነገሮች እንደ ሳሙና: በረኪና: ፍሊት: የአይጥ መርዝ: የፅዳት ኬሚካሎች እና ሌሎችም ለጤና ጠንቅ የሆኑ ሸቀጦች በሚሸጡባቸው ሱቆች በቀጥታ ለምግብነት የሚውሉትን እንጀራ እና ዳቦን መሸጥ ልክ እንዳልሆነ በመግለፅ ይህ ክልከላ መወሰኑን ገልጿል።

ክልከላው የህብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ ሲባል የተወሰነ እንደሆነ አመልክቷል። እንጀራ እና ዳቦ መሸጥ ያለባቸው በምግብ ቤቶች፣ በዳቦ ቤተች እና በባልትና ወይም ለዚሁ መሸጫነት በተፈቀደ ቦታ ብቻ መሆኑን አሳውቋል።

እንጀራ እና ዳቦ ያልተፈቀደላቸው ነጋዴዎች ሲሸጡ ከተገኙ አስፈላጊው የእርምት እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ማስጠንቀቂያ ተላልፏል። ህብረተሰቡ ለጤናው ሲል ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል።

ፈልግ

አስተያየትዎን ይተው