ከይር ቮክስ አፍሪካ

ዜና መዝናኛ

የአፍሪካ የመዝናኛ እና የመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ እድገት በፍጥነት ታይቷል

on | 2025-11-07 11:06:01 on2025-12-01 00:52:48

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin


የአፍሪካ የመዝናኛ እና የመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ እድገት በፍጥነት ታይቷል

PwC የተዘጋጀ አዲስ ሪፖርት መሠረት በአፍሪካ የመዝናኛ እና የመገናኛ ብዙሃን (E&M) ዘርፍ እድገት በፍጥነት እየጨመረ ነው።

ሪፖርቱ እንደሚያመለክተው፣ ናይጄሪያ በ2024 በመዝናኛ እና በሚዲያ ገበያዋ የ11.2% የእድገት መጠን አስመዝግባለች። እንዲሁም የናይጄሪያ የተቀናጀ አመታዊ እድገት (CAGR) እስከ 2029 ድረስ ወደ 7.2% እንደሚደርስ ትንበያው ይጠቁማል፤ በተጨማሪም በቅደም ተከተል ኬንያ (5.2%) እና ደቡብ አፍሪካ (3.5%) ይከተላሉ።

በዚህ እድገት የሚነሱ ቁልፍ አንቀሳቃሾች የሞባይል ኢንተርኔትና መረጃ አጠቃቀም፣ ቪዲዮ፣ የድምጽና ፖድካስት ይዘት፣ እና በማስታወቂያ የተደገፉ የዲጂታል ሞዴሎችን ያካትታሉ።

ይህ ሪፖርት የመዝናኛ ኢንዱስትሪው በአፍሪካ ውስጥ የዲጂታል ኢኮኖሚን በዋናነት የንግድ መሠረት ሆኖ እንሚያገለግል መረጃው ይጠቁማል። ይህም እድገት በአፍሪካ ውስጥ በንግድ፣ በኢንቨስትመንት እና በኢኮኖሚ ፖሊሲ ውሳኔዎች ላይ ጉልህ ድርሻ  እንዳለው ይነገራል።

Note:-

PwC = (PricewaterhouseCoopers) የዓለም አቀፍ የኦዲት፣ የፋይናንስና የኢኮኖሚ አማካሪ ኩባንያ ነው።)

ፈልግ

አስተያየትዎን ይተው