ከይር ቮክስ አፍሪካ

ዜና መዝናኛ

በሰርጉ ቀን ኮቱ ላይ ማስታወቂያ ሰርቶ የሰርግ ወጪውን የሸፈነው ሙሽራ

on | 2025-11-07 08:25:20

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin


በሰርጉ ቀን ኮቱ ላይ ማስታወቂያ ሰርቶ የሰርግ ወጪውን የሸፈነው ሙሽራ

ፈረንሳዊው ግለሰብ እጮኛውን ለማግባት ይፈልግና ለሰርጉ ወጪ የሚሆን ገንዘብ ያጥረዋል።
እጮኛው ደግሞ ሰርጉ በአደባባይ ተደግሶ እንዲጋቡ ትፈልጋለች።
ታድያ ይህ ሰው አንድ መላ መጣለት፤ ወዲያውም በኤክስ ገፁ ላይ ለሠርግ ቀኑ በሚለብሰው ኮት ላይ ለድርጅቶች የሚሆን የማስታወቂያ ቦታ እንደሚኖረው አስታወቀ።
ሀሳቡ በፍጥነት ይሰራጭና 26 ኩባንያዎች ማስታወቂያውን እንዲሰራላቸው ጠይቀውት በአጠቃላይም 10 ሺ ዶላር አገኘ።
በቅርቡም የጥንዶቹ ጋብቻ እንግዶች ፊት ሲፈፀም ግለሰቡ በቃሉ መሰረት የ26 የድርጅቶች አርማ የያዘውን ኮቱን ለብሶ የደስታውን ቀን አሳለፈ።
ታዲያ የሰርግ ወጪውን እንዲሸፍን ያስቻለው ይህ የሙሽራው እቅድ በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን አስገኝቶለታል።
አንድ የሥራ ፈጣሪ ድርጅትም የግለሰቡን ጠንክራ የሥራ አቅም ተመልክቶ በኒውዮርክ በሚገኝ ኩባንያ ውስጥ የሥራ ዕድል ሰጥቶታል።

ግለሰቡም ከሚወዳት ሴት ጋር ጋብቻ ለመፈፀም በአመጣው ሃሳብ ዘላቂ ገቢ የሚያገኝበትን እንጀራውንም ማብሰል ችሏል።

ምንጭ፡- ኢቢሲ መዝናኛ

ፈልግ

አስተያየትዎን ይተው