ከይር ቮክስ አፍሪካ

ዜና የሀገር ውስጥ

ብርሃን ባንክ በ2024/25 የሒሳብ ዓመት በአንድ አክሲዮን የ54.7% ትርፍ አስገኘ

on | 2025-10-30 19:42:18

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin


ብርሃን ባንክ በ2024/25 የሒሳብ ዓመት በአንድ አክሲዮን የ54.7% ትርፍ አስገኘ

ከይር ዜና - ብርሃን ባንክ አ.ማ. 16ተኛውን መደበኛ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ ጥቅምት 18 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ በሚሊኒየም አዳራሽ አካሄዷል። በጉባዔው ላይ የባንኩ ዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ  አቶ ኢሊጎ ለገሰ እ.ኤ.አ. ሰኔ 30 ቀን 2025 የተጠናቀቀውን የባንኩን ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለባለአክሲዮኖች አቅርበዋል። የቦርድ ሰብሳቢው በሪፖርታቸው፣ ባንኩ በዓለም አቀፍ እና በአገር አቀፍ ደረጃ የተከሰቱ የተለያዩ ኩነቶች ቢኖሩም በበጀት ዓመቱ አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ገልጸዋል።  

አቶ ኢሊጎ ባንኩ የ 2024/25 በጀት ዓመቱን ሲያጠናቅቅ ከግብር በፊት ብር 2.5 ቢሊዮን ትርፍ ማስመዝገብ መቻሉን ገልፀው ይህ ውጤት ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ66.5 በመቶ ወይም የብር 1 ቢሊዮን ብልጫ እንዳለው ገልጸዋል߹ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በበጀት ዓመቱ መጨረሻ የባንኩ አጠቃላይ ሀብት ብር 58.9 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን ይኽም ባለፈው ዓመት ተመዝግቦ ከነበረው ጋር ሲነጻጸር  የ28.1 በመቶ እድገት አሳይቷል።

የባንኩ አጠቃላይ ካፒታል ብር 8.5 ቢሊዮን በመድረስ ከባለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ20 በመቶ እድገት ማሳካቱን የገለጹ ሲሆን የተከፈል ካፒታሉን በተመለከተ ደግሞ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተቀመጠውን አንድ ባንክ ሊያሟላ የሚገባውን አነስተኛ የካፒታል መጠን በማሟላት ከብር 5 ቢሊዮን በላይ መድረሱን ገልጸዋል። ይህም በመሆኑ ብርሃን ባንክ እ.ኤ.አ. ሰኔ 30 ቀን 2025 በአንድ አክሲዮን የ54.7 በመቶ ትርፍ በማስገኘት የበጀት ዓመቱን በአመርቂ ስኬት ማጠናቀቅ መቻሉን አቶ ኢሊጎ አስረድተዋል።

ፈልግ

አስተያየትዎን ይተው