ዜና
አለም አቀፍ
ትራምፕ እና ጂንፒንግ ሐሙስ እንደሚገናኙ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ
on | 2025-10-29 11:48:06
Share: Facebook |
Twitter |
Whatsapp |
Linkedin
ስብሰባው በደቡብ ኮሪያዋ የወደብ ከተማ ቡሳን እንደሚካሄድ ሚኒስቴሩ በመግለጫው ጠቅሷል።
ፕሬዝዳንቶቹ "በቻይና-አሜሪካ ግንኙነት እና በሁለቱ ወገኖች የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ሃሳብ ይለዋወጣሉ" ተብሏል።
ትራምፕ ከእስያ-ፓሲፊክ የኢኮኖሚ ትብብር ጉባኤ በፊት ከጥቅምት 19 እስከ 20 ድረስ የሚካሄዱ ዝግጅቶችን ለመታደም ደቡብ ኮሪያን በመጎብኘት ላይ ይገኛሉ።
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ከሺ ጂንፒንግ ጋር ከተገናኙ በኋላ ከቻይና ጋር ስምምነት እንደሚጠብቁ ቀደም ሲል ተናግረው ነበር። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ውጥረት የነገሰበት የሁለቱ ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት በዋሽንግተን እና ቤጂንግ "የንግድ ጦርነት" ተብሎ ይገለፃል።
ሺ እና ትራምፕ ለመጨረሻ ግዜ የተገናኙት በአሜሪካው ፕሬዝዳንት የመጀመሪያ የሥልጣን ዘመን፤ በ2019 ነበር።