ከይር ቮክስ አፍሪካ

ዜና የሀገር ውስጥ

ምክር ቤቱ ነገ በጠቅላይ ሚኒስትር የሚቀርበውን የመንግስት አቋም በማዳመጥ የድጋፍ ሞሽን ያጸድቃል

on | 2025-10-27 07:34:20

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin


ምክር ቤቱ ነገ በጠቅላይ ሚኒስትር የሚቀርበውን የመንግስት አቋም በማዳመጥ የድጋፍ ሞሽን ያጸድቃል

ከይር ዜና:- የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ ጥቅምት 18 ቀን፣ 2018 ዓ.ም፤  በጠቅላይ ሚኒስትር የሚቀርበውን የመንግስት አቋም በማዳመጥ የድጋፍ ሞሽን ያጸድቃል ::                        

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ ነገ ጥቅምት 18 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በሚገኙበት 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን ይካሂዳል፡፡ 

በዚህ መደበኛ ስብሰባ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ክቡር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ መስከረም 26 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ለኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ ከምክር ቤቱ አባላት በሚቀርቡ ጥያቄዎች ላይ ክቡር የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡

ይህን ተከትሎም ምክር ቤቱ የመንግስትን አቋም በማዳመጥ የድጋፍ ሞሽኑን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በዕለቱ በሚካሄደው የምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሐይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች፣ የተፎካካሪ ፓርቲ ተጠሪዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የሚገኙ ሲሆን የስብሰባው ሙሉ ሂደትም በቀጥታ ስርጭት ለሕዝብ የሚተላለፍ ይሆናል፡፡

ፈልግ

አስተያየትዎን ይተው