on | 2025-10-25 18:58:09 on2025-12-01 01:38:27
Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin
የዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ በአማራ ክልል የሰብዓዊ ዕርዳታ ሥራዎች በቀጠለው የፀጥታ ችግርና የተደራሽነት ውስንነት ምክንያት ከፍተኛ የሆነ የሎጂስቲክስ ፈተናዎች እየገጠሙት መሆኑን አስታወቀ።
ድርጅቱ አማራ ክልልን በተመለከተ ባወጣው የሥራ ሁኔታ ግምገማ ሪፖርት፣ በተለይም በ #መተማ እና በ #ምሥራቅ_አማራ አካባቢዎች ያለው የጸጥታ ችግር የዕርዳታ አቅርቦቶችን ትራንስፖርት በእጅጉ እያዘገየ መሆኑን ጠቁሟል።
ሪፖርቱ፣ በተለያዩ አካባቢዎች የንግድ ትራንስፖርት አገልግሎት እጥረት መኖሩን በመጥቀስ፣ ለተቸገሩ ማኅበረሰቦች ዕርዳታ በወቅቱ እንዳይደርስ እንቅፋት እየፈጠረ መሆኑን አስረድቷል።
የዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ ምንም እንኳ እነዚህ ገደቦች ቢኖሩም፣ የሎጂስቲክስ ክላስተር በግጭት ባለበት ክልል ውስጥ የሰብዓዊ አጋሮች ሥራቸውን መቀጠል እንዲችሉ ትራንስፖርትን፣ ማከማቻን እና ቅንጅትን ጨምሮ የጋራ አገልግሎቶችን ማቅረቡን መቀጠሉን ገልጿል።
ሪፖርቱ እንደሚያመለክተው፣ የሎጂስቲክስ ክላስተር በመስከረም ወር 2018 172 ኪዩቢክ ሜትር ሰብዓዊ ዕርዳታ ወደ ክልሉ እንዲላክ አመቻችቷል። ይህም ከጥር ወር 2017 ዓ/ም ጀምሮ የተጓጓዘውን አጠቃላይ መጠን 7,711 ኪዩቢክ ሜትር ያደርሰዋል ብሏል። ቀጣይነት ያለው ጥረት እየተደረገ መሆኑን የገለጸው ሪፖርቱ፣ የጸጥታው ሁኔታ ተለዋዋጭ በሆነበት ወቅት የዕርዳታ አቅርቦትን ለማረጋገጥ ተሽከርካሪዎች በአንድ ላይ መንቀሳቀሳቸው (ኮንቮይ ኦፕሬሽኖች) ወሳኝ መሆኑን ጠቅሷል።
በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ፣ 11 የጭነት መኪኖችን ያቀፉ ሦስት ሰብዓዊ እርዳታ ጭነቶች ወደ አማራ ክልል እንዲገቡ እና በክልሉ ውስጥ እንዲንቀሳቀሱ ተደርጓል ተብሏል። በቅንጅት ተሽከርካሪዎች በአንድ ላይ መንቀሳቀሳቸው የአጋሮች ተሽከርካሪዎች ወደ ተለያዩ የክልሉ ክፍሎች በሰላም እንዲንቀሳቀሱ በመደገፍ ረገድ ወሳኝ ነበር ያለው ክላስተሩ፣ ይህም የሕይወት አድን ፕሮግራሞች እንዲቀጥሉ አስችሏል ብሏል።
በወላይታ ብሔር ዘንድ ልዩ ቦታ የሚሰጠው "ጊፋታ”
በቶኪዮ የወርቅ መርገም አልሰበር ያላት ኢትዮጲያ