on | 2025-10-25 18:56:12
Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin
118ኛው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቀን "የማትደፈር ሀገር የማይበገር ሠራዊት" በሚል መሪ ቃል በልዩ ልዩ ክንውኖች እየተከበረ ይገኛል፡፡
በክብረ በዓሉ ላይ የዕለቱ የክብር እንግዳ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የመከላከያ ሚኒስትር ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሃመድ፣ ጄኔራል መኮንኖች፣ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች፣ የመከላከያ የክብር አባላት፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የሠራዊት አባላት ታድመዋል።
የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሐመድ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፤ ዛሬ ኩሩ ሀገርን ለሚጠበቁ ኩሩ የመከላከያ ሰራዊት ክብር የምንሰጥበት ቀን ነው ብለዋል።
የመከላከያ ሰራዊት የኢትዮጵያን ክብርና ማንነት የሚጠብቅ፣ የሰላምና የሉዓላዊነት ጠባቂ እንዲሁም የሀገሪቱን እጣ ፋንታ የሚወስን ኃይል ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ የጸነችው ጋሻዎቿ ፈጽሞ ስላልተሸነፉ መሆኑን ገልጸው፤ አሁንም እድገቷን ከፍ አድርጋ እንደምትቀጥል ምንም ጥርጥር የለንም ሲሉ አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያን የመጠበቅ ግዴታ ጊዜ የማይሽረው በየትውልዱ የሚሻገር ዘላቂ ተልዕኳችን ነው ሲሉ አስገንዝበዋል።
በወላይታ ብሔር ዘንድ ልዩ ቦታ የሚሰጠው "ጊፋታ”
በቶኪዮ የወርቅ መርገም አልሰበር ያላት ኢትዮጲያ