ከይር ቮክስ አፍሪካ

ዜና የሀገር ውስጥ

ስምረት ፓርቲ በመስራች ጉባኤው አቶ ጌታቸው ረዳን በፕሬዚዳንትነት መርጧል

on | 2025-10-25 18:53:26

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin


ስምረት ፓርቲ በመስራች ጉባኤው አቶ ጌታቸው ረዳን በፕሬዚዳንትነት መርጧል

መስራች ጉባኤውን ያካሄደው የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ስምረት(ስምረት) ፓርቲ አቶ ጌታቸው ረዳን የፓርቲው ፕሬዚዳንት በማድረግ መርጧል፡፡

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ስምረት(ስምረት) ፓርቲ ከፍተኛ የፓርቲው አመራሮች እና መሥራች አባላቱ በተገኙበት የመጀመሪያ ጉባዔውን አካሂዷል።

በጉባኤው መክፈቻ ንግግር ያደረጉት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ ፓርቲው ለትግራይ ሕዝብ ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት በሚሆን መልኩ በአዲስ አስተሳሰብ የተዋቀረ መሆኑን መግለጻቸውን የኢቢሲ ዘገባ ያመላክታል። 

የብልፅግና ፓርቲን ወክለው የተገኙት አቶ መለስ ዓለም፣ አዳዲስ የፖለቲካ ፓርቲዎች በትብብር መሥራታቸው ኢትዮጵያ የጀመረችው አዲስ የፖለቲካ አካሄድ ማሳያ ነው ሲሉ ገልጸዋል። 

ስምረት ፓርቲም ለትግራይ ሕዝብ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ተሳትፎ አዲስ ሐሳብ ይዞ የመጣ ፓርቲ እንደመሆኑ ከብልፅግና ፓርቲ ጋር ያለው የፖለቲካ እና የአቋም ልዩነት እንዳለ ሆኖ ሀገራችን ለጀመረችው ጉዞ የሚኖረው አበርክቶ ግን የጎላ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ፓርቲው አቶ ጌታቸው ረዳን ፕሬዚዳንት በተጨማሪም ነጋ አሰፋን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት፣ ሃፍቱ ኪሮስ ምክትል ፕሬዚዳንት እንዲሁም ሰብለ አሰፋን የፓርቲው ፅህፈት ቤት ኃላፊ በመሆን ተመርጠዋል።

ፓርቲው መስራች ጉባኤውን ሲያካሂድ ከፓርቲው ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንት በተጨማሪ ሰባት ጉዳይ ፈፃሚ ኮሚቴ አባላት እና 31 የምክር ቤት አባላትን መምረጡም ተገልጿል፡፡

ፓርቲው የቁጥጥር ኮሚሽን እና ኢንስፔክሽን ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር መርጧል፡፡

በዚሁ በፓርቲው የምሥረታ ጉባኤ ላይ የተገኙ አባላትም የትግራይ ሕዝብ በተለይም ወጣቱ ለውጥ እንደሚፈልግ መናገራቸውም በዘገባው ተጠቅሷል። 

ፈልግ

አስተያየትዎን ይተው