ከይር ቮክስ አፍሪካ

ዜና የሀገር ውስጥ

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ላይ ለመቀመጥ ብሔራዊ መታወቂያ (National ID) ቅድመ ሁኔታ ተደረገ።

on | 2025-10-22 21:39:59

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin


የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ላይ ለመቀመጥ ብሔራዊ መታወቂያ (National ID) ቅድመ ሁኔታ ተደረገ።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት "ብሔራዊ መታወቂያ (National ID) ለፈተና ለመቀመጥ ቅድመ ሁኔታ ነው" ብሏል።

"ማንኛውም የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ብሔራዊ መታወቂያ (National ID) ከፈተና ምዝገባ ቀድሞ ማውጣትና በእጁ መያዝ ይገባዋል " ሲል አሳውቋል።

"ብሔራዊ መታወቂያ (National ID) የሌለው ተማሪ ለፈተና መመዝገብ ሆነ በማንኛውም ሁኔታ መፈተን አይችልም" ሲል አስገንዝቧል።

ተማሪዎች የብሔራዊ መታወቂያ (National ID) ይዘው እንዲገኙ  ለቤተሰብ; ለመምህራንና የትምህርት አመራሮች; የሚዲያ አካላት ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

ፈልግ

አስተያየትዎን ይተው