ከይር ቮክስ አፍሪካ

ዜና የሀገር ውስጥ

ብሔራዊ ባንክ ህገወጥ የሐዋላ ገንዘብ አስተላላፊዎችን አስጠነቀቀ

on | 2025-10-22 20:18:19 on2025-12-01 01:37:00

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin


ብሔራዊ ባንክ ህገወጥ የሐዋላ ገንዘብ  አስተላላፊዎችን አስጠነቀቀ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ፣ መንግሥት በህገወጥ የሐዋላ ገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች ላይ ከባድ እርምጃ ይወስዳል ሲሉ አስጠነቀቁ፡፡

ባንኩ ከውጭ ሀገር ከሚገኙ ሀዋላ አስተላላፊ ድርጅቶችና ከንግድ ባንኮች ጋር በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮችና በሚወሰዱ ህጋዊ ርምጃዎች ዙሪያ ውይይት መደረጉ ተጠቁሟል።

ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ ውይይቱን አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ÷ ሐዋላ አስተላላፊ ድርጅቶች በህጋዊ መንገድ እንዲሰሩ መንግስት ድጋፍ በሚያደርግባቸው ጉዳዮች ላይ ምክክር መደረጉን ገልጸዋል፡፡

መንግስት ሁሉም የሐዋላ ገንዘብ አስተላላፊዎች ወደ ህጋዊ መንገድ እንዲገቡ በተደጋጋሚ ያቀረበውን ጥሪ ያልተቀበሉ አንዳንድ ድርጅቶች መኖራቸውን ጠቁመዋል፡፡

ብሔራዊ ባንክ በእነዚህ ህገወጥ የሀዋላ ገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች ላይ በጥናትና በመናበብ ላይ የተመሰረተ ጠንካራ እርምጃ እንደሚወስድ ማስጠንቀቃቸውን የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡

ፈልግ

አስተያየትዎን ይተው