ጋዛ ዉስጥ እንደታገቱ የሞቱ የእስራኤል የታጋቾች አስከሬኖች ፍለጋን የሚያግዙ 81 የአደጋ ጊዜ እርዳታ ሰራተኞች ወደ ጋዛ መላኳን ቱርክ አስታወቀች።
የቱርክን መከላከያ ሚኒስቴርን ምንጭ ጠቅሶ AFP እንደዘገበው ባለሞያዎቹ እገዛ የሚያደርጉት እስካሁን ያልተገኘ የ19 ታጋቾችን አስከሬን ፍለጋን ነው።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንዳለው የሰዎቹ ተልዕኮ ሰብዓዊ እርዳታ ማስተላለፍ፣ አስከሬኖችን መፈለግ እና የተኩስ አቁሙን ማስጠበቅ ነው።
የቱርክ የአደጋ ጊዜ እርዳታ ሠራተኞች ከቱርክ በተጨማሪ ሶማሊያ የፍልስጤም ግዛቶች ኢኳዶርና በፊሊፒንስ ጨምሮ ከ50 በሚበልጡ ሀገራት የሕይወት አድንና የሰብአዊ እርዳታ ተልዕኮዎችን አከናውነዋል።