on | 2025-10-17 12:21:09
Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin
የኬንያውን ፖለቲከኛ የራይላ ኦዲንጋን አስከሬን የያዘው የሬሳ ሳጥን ዛሬ ከህንድ ወደ ኬንያ ከመጣ በኋላ ለህዝብ እይታ በተቀመጠበት በአንድ ስታድዮም የፀጥታ ኃይሎች ፣ጥይትና አስለቃሽ ጭስ ሲተኮሱ በ10 ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በፍርሃት መሸሻቸውን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት AFP ዘገበ።
ሰዎቹ የሸሹትም የፀጥታ ኃይሎች ፣በስታድዮሙ ለባለሥልጣናት እና ለታዋቂ ሰዎች የተያዘውን ስፍራ ሰብረው ለመግባት የሞክሩ ሰዎችን ለመበተን መተኮስ ከጀመሩ በኋላ ነው። በAFP ዘገባ መሠረት በካሳራኒ ስታድዮም ሀዘናቸውን ለመግለፅ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገኝተዋል። የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ጋዜጠኞች፣ ቢያንስ ሦስት ሰዎች መቁሰላቸውን ፤ከመካከላቸው አንዱም ጭንቅላቱ ላይ ከባድ ጉዳት እንደደረሰበት አይተዋል።
ደጋፊዎቻቸው ባባ ወይም አባት ብለው የሚጠሯቸው የኦዲንጋ አስከሬን በመጀመሪያ ወደ ሀገሪቱ ምክር ቤት ሊወሰድ ነበር ። ሆኖም ደጋፊዎቻቸው በምክር ቤቱ አጥር ላይ መንጠላጠል በመጀመራቸው ባለሥልጣናት ከከተማዋ ወጣ ብሎ ወደሚገኘው ወደ ካሳራኒ ስታድዮም እንዲወሰድ ወሰኑ። ወደ ስታድዮሙ የሚወስደው ዋነኛው አውራ ጎዳናም በወቅቱ በደጋፊዎቻቸው ተጥለቅልቆ ነበር።
የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በኦዲንጋ ሞት የሰባት ቀናት
ሀዘን አውጀዋል። የኬንያ መንግሥት ቴሌቪዥን ኦዲንጋ በሚቀበሩበት ቦንዶ በሚባለው ምዕራብ ኬንያ በሚገኘው የዘር ሐረጋቸው መቀመጫም
በርካታ ሰዎች ተሰብስበው አሳይቷል።
በወላይታ ብሔር ዘንድ ልዩ ቦታ የሚሰጠው "ጊፋታ”
በቶኪዮ የወርቅ መርገም አልሰበር ያላት ኢትዮጲያ