on | 2025-10-17 12:11:32
Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin
በአፍጋኒስታን ፣ በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ፣በሄይቲ በሶማሊያ በሱዳንና ደቡብ ሱዳን ቁጥራቸው ወደ 14 ሚሊዮን የሚጠጋ ሰዎች በከባድ ረሀብ እየተሰቃዩ ነው ሲል የዓለም ምግብ ድርጅት አስታወቀ።
ድርጅቱ ዛሬ ሮም በሚገኘው ጽህፈት ቤቱ የዓለም የምግብ ቀን ባሰበበት ስነ ስርዓት ላይ ባወጣው ዘገባ ሰዎቹ በረሀብ የሚሰቃዩት በዓለም አቀፍ የምግብ እርዳታ መቀነስ ምክንያት መሆኑን አስታውቋል።
ለድርጅቱ ከፍተኛ እርዳታ በመስጠት ቀዳሚውን ስፍራ ትይዝ የነበረው ዩናይትድ ስቴትስ በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር የውጭ እርዳታን መሰረዟን አስታውቋል። ሌሎች ዋነኛ የሚባሉ ለጋሽ ሀገራትም የልማትና ሰብዓዊ እርዳታን መቀነሳቸውን ገልጿል።
ድርጅቱ እንዳለው በጎርጎሮሳዊው 2025፣ ከቀደመው ዓመት በ40 በመቶ ያነሰ እርዳታ ነው ያገኘው። በዚህ
የተነሳም በጎርጎሮሳዊው 2024 ዓ.ም. 10 ቢሊዮን ዩሮ የነበረው የድርጅቱ በጀት በዚህ ዓመት ወደ 6.4 ቢሊዮን ዶላር ዝቅ ብሏል።
በወላይታ ብሔር ዘንድ ልዩ ቦታ የሚሰጠው "ጊፋታ”
በቶኪዮ የወርቅ መርገም አልሰበር ያላት ኢትዮጲያ