ከይር ቮክስ አፍሪካ

ዜና የሀገር ውስጥ

በአማራ ክልል 2445 ትምህርት ቤቶች ዝግ መሆናቸው ተገለጸ፣ ከአንድ ሺ በላይ የሚሆኑት ከታለመላቸው አላማ ውጪ እየዋሉ ነው ተብሏል

on | 2025-10-07 12:38:57

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin


በአማራ ክልል 2445 ትምህርት ቤቶች ዝግ መሆናቸው ተገለጸ፣ ከአንድ ሺ በላይ የሚሆኑት ከታለመላቸው አላማ ውጪ እየዋሉ ነው ተብሏል

በአማራ ክልል ከሚገኙ  11,069 ትምህርት ቤቶች ውስጥ የተማሪዎች ምዝገባ ያከናወኑት 8624 ያህሉ ብቻ መሆናቸው ተገለጸ። 2445 ያህሉ ምንም አይነት የተማሪዎች ምዝገባ እንዳልተከናወነባቸው ተጠቁሟል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ በማስመልከት በአዲስ አበባ ባዘጋጀው ውይይት ላይ የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊው ዶ/ር መንገሻ ፈንታው እንደተናገሩት፤ እስከ መስከረም 20/2018 ድረስ በክልሉ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች  ውስጥ መመዝገብ ከነበረባቸው 7.4 ሚሊዮን  ተማሪዎች ውስጥ 3.96 ሚሊዮን የሚሆኑት ምዝገባ አላካሄዱም።

የሰሜኑን ጦርነት ጨምሮ በክልሉ እየተካሄደ ባሉ ግጭቶች 6154 ትምህርት ቤቶች መፍረሳቸውን እና ከእነዚህም ውስጥ 1980 የሚሆኑት የፈረሱት በአሁኑ ወቅት በክልሉ እየተካሄዱ ባሉ ግጭቶች ምክንያት መሆኑን በመግለፅ የትምህርት ዘርፉን እንደ መያዣ  በመጠቀም የራሱን ፍላጎት እያስፈፀመ ያለን አካል የሐይማኖት አባቶች ሊያስቆሙት ይገባል ሲሉ ማሳሰባቸው ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

ፈልግ

አስተያየትዎን ይተው