ከይር ቮክስ አፍሪካ

ዜና የሀገር ውስጥ

ዓለም ባንክ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በከፍተኛ ኪሳራ እና ፍትሐዊ ባልሆነ ውድድር እየተፈተነ መሆኑን አሳወቀ

on | 2025-10-06 19:14:00 on2025-12-01 00:52:00

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin


ዓለም ባንክ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በከፍተኛ ኪሳራ እና ፍትሐዊ ባልሆነ ውድድር እየተፈተነ መሆኑን አሳወቀ

የዓለም ባንክ እና የዲጂታል ልማት አጋርነት በቅርቡ ባወጡት "የኢትዮጵያ የቴሌኮም ገበያ ግምገማ" ሪፖርት መሠረት፣ አዲስ የገባው የቴሌኮም ኩባንያ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከፍተኛ የገበያ ፈተናዎችን እየገጠመው ነው። 

ሳፋሪኮም ከሰረ?

ሪፖርቱ ሳፋሪኮም በ2024 በጀት ዓመት 325 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ እንደደረሰበት ገልጿል፤ አመታዊ ገቢው (53.6 ሚሊዮን ዶላር) ለፈቃድ ክፍያው ወጪ እንኳን በቂ አይደለም ይላል።

ለዚህ ዋናው ምክንያት ደግሞ በመንግሥት ከተያዘው ኢትዮ ቴሌኮም ጋር እኩል ያልሆነ የመወዳደሪያ ሜዳ አለመፈጠሩ ነው። ኢትዮ ቴሌኮም የፈቃድ ክፍያ አለመክፈሉ እና ሳፋሪኮም ከኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች በሚደረጉ ጥሪዎች አማካኝነት በወር 1.6 ሚሊዮን ዶላር እንዲያጣ የሚያደርግ የጥሪ ዋጋ (MTR) ቅናሽ ማድረጉ የውድድሩን ፍትሐዊነት ጎድቶታል። 

በተጨማሪም ኢትዮ ቴሌኮም የሳፋሪኮም መተግበሪያዎችን አግዷል እና በቴሌብር የዳታ ግዢ ላይ ቅናሽ በማድረግ ደንበኞችን በኔትወርኩ ላይ እንዲቆዩ ያደርጋል ተብሏል። 

ዓለም ባንክ እነዚህን ችግሮች ለመፍታት የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን (ECA) እንደ ስታርሊንክ ላሉ የሳተላይት ኦፕሬተሮች ፈቃድ እንዲሰጥ፣ የፍቃድ አሰጣጥ ሥርዓቱን እንዲያስተካክል እና በፍትሐዊ ባልሆነ ውድድር ዙሪያ የተነሱትን ስጋቶች በጥልቀት እንዲመረምር መክሯል።



ፈልግ

አስተያየትዎን ይተው