ከይር ቮክስ አፍሪካ

ዜና አለም አቀፍ

በምዕራብ ሱዳን በከበባ ውስጥ በምትገኘው የኤል ፋሽር ከተማ የፈጥኖ ደራሽ ወይም የአር ኤስ ኤፍ ኃይሎች ባደረሷቸው ጥቃቶች በአስር ቀናት ውስጥ 91 ሰላማዊ ሰዎች ተገደሉ ።

on | 2025-10-04 07:05:50 on2025-12-01 00:52:01

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin


በምዕራብ ሱዳን በከበባ ውስጥ በምትገኘው የኤል ፋሽር ከተማ የፈጥኖ ደራሽ ወይም የአር ኤስ ኤፍ ኃይሎች ባደረሷቸው ጥቃቶች በአስር ቀናት ውስጥ 91 ሰላማዊ ሰዎች ተገደሉ ።

በብሔራዊ ጦሩ እና በአር ኤስ ኤፍ ኃይሎች መካከል በአካባቢው የሚደረገው  ዉጊያ መባባሱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል።

በመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ጉዳይ ኃላፊ ቮልከር ቱርክ ትናንት ሐሙስ እንዳሉት ከመስከረም 9 ቀን እስከ 19 በነበሩ አስር ቀናት ውስጥ በዳራጃ ኦዉላ ከተማ እና በዙሪያው ባሉ መንደሮች የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች በከባድ መሳሪያ እና በድሮን የታገዘ ተከታታይ ጥቃት ፈጽመዋል።

«በኤል ፋሽር የተፈጸሙ ጥቃቶች በጭካኔ የተሞሉ ናቸው» ያሉት ኃላፊው «መጠነ ሰፊ እና ብሔር ተኮር ጥቃቶችን ለመከላከል» አስቸኳይ እርምጅ መወሰድ እንዳለበት አሳስበዋል።

አር ኤስ ኤፍ በከተማዋ ባደረሰው የቅርብ ጊዜ ጥቃቱ ባስወነጨፈው  ሚሳኤል ሶስት ሴቶችን ጨምሮ 16 ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች 21 ሰዎች መቁሰላቸውን የሱዳን ሐኪሞች ኔትወርክ ባለፈው ረቡዕ አስታውቋል።  በጥቃቱ ከቆሰሉት ውስጥ አምስት ህጻናት ይገኙበታል።

ጥቃቱን በተመለከተ ለፈጥኖ ደራሹ ቡድን ጥያቄ አቅርቦ ወዲያው መልስ አለማግኘቱን አሶሽየትድ ፕረስ ዘግቧል።  

ፈልግ

አስተያየትዎን ይተው