on | 2025-10-04 06:44:36 on2026-03-01 17:49:34
Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin
6ኛው የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤትና የፌዴሬሽን ም/ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ሰኞ መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።
የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የአንድ ዓመት የሥራ ጊዜ ከመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ መሆኑ ተደንግጓል፡፡
በዚህ መሰረትም የ6ኛው ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የተጠናቀቀ ሲሆን ÷ 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ ሥርዓትም ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በተገኙበት በመጪው ሰኞ ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል፡፡
ፕሬዚዳንት ታዬ ለሁለቱ ምክር ቤቶች ዓመታዊ ሥራቸውን እንደጀመሩ በማብሰር የፌደራል መንግስቱን ዓመታዊ ዕቅድ የሚያቀርቡ ይሆናል፡፡