የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቤ ሳኖ ፕሪቶሪያ ከተማ ሲደርሱ በደቡብ አፍሪካ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ደሊል ከድር፣ ዲፕሎማቶችና ሌሎች አካላት አቀባበል አድርገውላቸዋል።

አቤ ሳኖ በደቡብ አፍሪካ በሚኖራቸው ቆይታ ከተለያዩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ከሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር አብሮ መስራት በሚቻልበት ሁኔታዎች ላይ ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

ከዚህም በተጨማሪ በደቡብ አፍሪካ ከተሞች ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር አካታች የፋይናንስ አገልግሎት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም ወደ ሀገር ቤት በሚልኩት የውጭ ምንዛሬና የኢንቨስትመንት ፍላጎት ጋር የተጣጣመ የፋይናንስ ተጠቃሚነት እና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ገንቢ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።