ከይር ቮክስ አፍሪካ

ከይር ቮክስ አፍሪካ

ዜና የሀገር ውስጥ

የእስራኤሉ ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ ለይፋዊ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

on | 2026-02-25 06:14:58 on2026-03-01 14:08:35

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin


የእስራኤሉ ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ ለይፋዊ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ – የእስራኤል ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ ለይፋዊ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዝዳንቱ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) እና ሚኒስትር ዴኤታው አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ በክብር አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ በአዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታ የኢትዮጵያና እስራኤል መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ከኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ ተገልጿል።

ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ውይይቶቹ በዲፕሎማሲ፣ በኢኮኖሚ፣ በቴክኖሎጂ፣ በእርሻ እና በሌሎች የጋራ ጥቅም ዘርፎች ላይ ይተኮራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ጉብኝቱ የሁለቱን አገራት ታሪካዊ ግንኙነት በአዲስ ደረጃ ለማሳደግ እንደሚያግዝ ተጠቁሟል።

Tags: Ethiopia, Israel, Diplomacy, Addis Ababa, Foreign Affairs


አስተያየትዎን ይተው