ከይር ቮክስ አፍሪካ

ከይር ቮክስ አፍሪካ

ዜና የሀገር ውስጥ

አዋሽ ኢንሹራንስ የኢትዮጵያ አየር መንገድን የጉዞ መድን ጨረታ አሸነፈ

on | 2026-02-22 18:35:42 on2026-03-01 15:48:55

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin


አዋሽ ኢንሹራንስ የኢትዮጵያ አየር መንገድን የጉዞ መድን ጨረታ አሸነፈ

ለሦስት ዓመት ውል ተፈራረመ

አዲስ አበባ፡– አዋሽ ኢንሹራንስ የየኢትዮጵያ አየር መንገድን የጉዞ መድን አገልግሎት ለመስጠት የተካሄደውን ጨረታ በማሸነፍ ለሦስት ዓመት የሚቆይ ውል መፈራረሙ ተገለጸ።

አየር መንገዱ በሞባይል መተግበሪያው በመታገዝ ለተጓዥ ደንበኞቹ የጉዞ መድን ሽፋን አገልግሎት ለመስጠት ያወጣው ጨረታ በኢንሹራንስ ዘርፍ ያሉ ተቋማት በስፋት ተሳትፎ እንዳገኘ ተመልክቷል። ከተሳተፉት ኩባንያዎች መካከል አራት ተወዳዳሪዎች ወደ መጨረሻ ዙር ከደረሱ በኋላ፣ አዋሽ ኢንሹራንስ ባቀረበው የዋጋና የአገልግሎት ጥራት መሠረት አሸናፊ ሆኖ ተመርጧል።


በተፈረመው ስምምነት መሠረት ኩባንያው ለአየር መንገዱ ተጓዥ ደንበኞች በጉዞ ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ የጤና እክሎችና ሌሎች ያልተጠበቁ ችግሮች የመድን ሽፋን ይሰጣል። እያንዳንዱ የመድን ሽፋን በጥቅልና በተናጠል የሚቀርብ ሲሆን፣ የድንገተኛ ሕክምና ወጪዎችን ጀምሮ በጉዞ ላይ የሚከሰቱ የተለያዩ አደጋዎችን እንዲሸፍን ይደርሳል።

እንዲሁም በአጋጣሚ የሞት አደጋ ቢከሰት የአስከሬን ማጓጓዣ ወጪዎችን የሚሸፍን የተለየ የመድን ሽፋን መካተቱ ታውቋል። በተጨማሪም ከበረራ መዘግየት ወይም በረራ ማምለጥ ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ ያልተጠበቁ እንግልቶችና ወጪዎች በዚህ የጉዞ መድን ሽፋን ውስጥ መካተታቸው ተገልጿል።

አገልግሎቱ በይፋ ወደ ሥራ የገባ ሲሆን፣ በአየር መንገዱ ዲጂታል መስመሮች በቀላሉ ለደንበኞች እንዲደርስ ዝግጅት መደረጉ ታውቋል። ይህም ተጓዦች በጉዞቻቸው ወቅት የሚያጋጥማቸውን አደጋዎች በመቀነስ የተሻለ የአገልግሎት ዋስትና እንዲያገኙ ያስችላል።


አስተያየትዎን ይተው