ከይር ቮክስ አፍሪካ

ከይር ቮክስ አፍሪካ

ዜና የሀገር ውስጥ

የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ለባንኮች አዲስ መመሪያ ሰጠ

on | 2026-02-22 10:20:44 on2026-03-01 17:26:22

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin


የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ለባንኮች አዲስ መመሪያ ሰጠ

አዲስ አበባ፣ — የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በጻፈው ደብዳቤ መሠረት፣ ከየካቲት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በባንኮች የሚፈጸሙ ግብይቶች ላይ በደንብ ቁጥር 576/2018 ዓ.ም በተደነገገው የማስከፈያ ስሌት መሠረት ክፍያ እንዲሰበሰብ ማሳሰቢያ ለሁሉም ባንኮች ሰጥቷል። የሚሰበሰቡት ክፍያዎች በብሔራዊ ባንክ በተያዘው የኢትዮጵያ አደጋ ስጋትና ምላሽ ፈንድ ሂሳብ ገቢ እንዲደርሱ ተገልጿል።

በዚህ መሠረት፣ አዋሽ ባንክ ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ ከሚሰጠው ማንኛውም አይነት መደበኛ ብድር ላይ የብድር መጠኑ 1 በመቶ ተጨማሪ ክፍያ እንደሚሰበስብ አስታውቋል። በተጨማሪም በባንኩ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች ከሚከፍሉት የአገልግሎት ክፍያ ላይ 5 በመቶ ተጨማሪ እንደሚጨመር ገልጿል።

ባንኩ በሰጠው መግለጫ መሠረት፣ የሚሰበሰቡት ክፍያዎች በተመረጠው የፈንድ ሂሳብ ገቢ እንዲሆኑ እንደሚደረግ አመልክቷል።

ደንበኞች በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት አቅራቢያቸውን የባንኩን ቅርንጫፍ ወይም ወደ 8980 በመደወል የጥሪ ማዕከሉን ማግኘት እንደሚችሉ ተጠቁሟል።


አስተያየትዎን ይተው