on | 2026-02-17 13:45:25 on2026-03-01 17:26:02
Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin
አዲስ አበባ - ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዛሬ በቦሌ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት ተገኝተው ለይፋዊ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡትን የቱርክዬ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ኤርዶጋን ተቀብለዋል።
ይህ የመንግሥታዊ ጉብኝት በኢትዮጵያና ቱርኪዬ መካከል በቅርብ ዓመታት እየጠነከረ የመጣውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት የሚያጎላ መሆኑን መንግሥታዊ ምንጮች ገልጸዋል። በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በዲፕሎማሲ መስኮች ያለው ትብብር እንደሚቀጥልና እንደሚጠናከር ይጠበቃል።
በተጨማሪም የፕሬዝዳንት ኤርዶዋን ጉብኝት አዲስ አበባ እንደ ክልላዊና አህጉራዊ የዲፕሎማሲ ማዕከል ያላትን ሚና ዳግመኛ የሚያረጋግጥ መሆኑን ባለሙያዎች ይጠቁማሉ።