ከይር ቮክስ አፍሪካ

ከይር ቮክስ አፍሪካ

ዜና የሀገር ውስጥ

“አፍሪካ በጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ ወንበር አለማግኘቷ ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው ነው” - አንቶኒዮ ጉቴሬዝ

on | 2026-02-14 15:59:49

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin


“አፍሪካ በጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ ወንበር አለማግኘቷ ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው ነው” - አንቶኒዮ ጉቴሬዝ

አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ ወንበር አለማግኘቷ ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለውና የታሪክ ስህተት መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ገለጹ።

በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው 39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት ዋና ጸሐፊው፤ የአፍሪካ ጥንካሬ የሚመነጨው በራሱ በሚተማመን እና በተባበረ ሕብረት መሆኑን ተናግረዋል። 

አህጉሪቱ በዓለም አቀፍ የጸጥታው ምክር ቤት ውስጥ ቋሚ ወንበር አለማግኘቷ የዓለም አቀፉን ተቋም ፍትሐዊነት ጥያቄ ውስጥ የሚጥል መሆኑን ጠቅሰው፤ ስለ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ውሳኔ በሚተላለፍበት ጠረጴዛ ዙሪያ አፍሪካ የግድ መገኘት እንዳለባት አጽንኦት ሰጥተዋል።

አፍሪካ በዓለም አቀፍ መድረኮች የሚገባትን ድምፅ እንድታገኝ የሚደረገውን ጥረት ድርጅታቸው እንደሚደግፍም አመልክተዋል።


አስተያየትዎን ይተው