ከይር ቮክስ አፍሪካ

ከይር ቮክስ አፍሪካ

ዜና የሀገር ውስጥ

ፌደራል ፖሊስ አዲስ የተሽከርካሪ ሰሌዳ አስጀመረ

on | 2026-02-04 09:03:48

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin


ፌደራል ፖሊስ አዲስ የተሽከርካሪ ሰሌዳ አስጀመረ

አዲስ አበባ — የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከ50 ዓመታት በላይ ሲያገለግል የነበረውን የተሽከርካሪ ሰሌዳ በቴክኖሎጂ የተደገፈ አዲስ ሰሌዳ ቀይሯል።

የፌደራል ፖሊስ ሎጂስቲክስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር እሸቱ ፊጣ እንዳሉት፣ የቀድሞው ሰሌዳ ወጥነት የሌለውና ለቁጥጥር አመቺ አልነበረም።

አዲሱ ሰሌዳ ከመረጃ ቋት ጋር የተጣመረ፣ በህገወጥ መንገድ የማይባዛ ሚስጥራዊ መለያዎችን የያዘ ሲሆን፣ የቁጥጥርና የስራ እንቅስቃሴን ቀልጣፋ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተገልጿል።

እንዲሁም የወንጀል ምርመራና ክትትል ስራን ለማሳለጥ እና ለህዝብ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት አጋዥ መሆኑ ተጠቅሷል።

ይህ እርምጃ ከኢትዮጵያ የዲጂታል 2030 ግብ ጋር የተዛመደ መሆኑንም ፌደራል ፖሊስ አመልክቷል።


አስተያየትዎን ይተው