ከይር ቮክስ አፍሪካ

ከይር ቮክስ አፍሪካ

ዜና የሀገር ውስጥ

ኢትዮጵያ ከዓለም በፍጥነት እያደጉ ካሉ ሀገራት አንዷ ናት - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

on | 2026-02-03 08:11:07 on2026-03-01 19:05:28

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin


ኢትዮጵያ ከዓለም በፍጥነት እያደጉ ካሉ  ሀገራት አንዷ ናት - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

አዲስ አበባ:- ኢትዮጵያ በፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ከዓለም ቀዳሚ ከሆኑ አገራት ተርታ መሰለፏን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ፒ.ኤች.ዲ) አስታወቁ።

የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) እንደተነበየው፣ ኢትዮጵያ በ2026 የ9.3 በመቶ ዕድገት እንደምታስመዘግብ ይጠበቃል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ፒ.ኤች.ዲ) ዛሬ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 10ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በንግግራቸውም የኢትዮጵያን ወቅታዊ የኢኮኖሚ ጉዞ በሚመለከት አበይት ነጥቦችን አንስተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት በ2025 በዓለም ላይ በፍጥነት ከሚያድጉ 10 አገራት መካከል አምስቱ ከአፍሪካ ሲሆኑ፣ ኢትዮጵያ በዚህ ዝርዝር ውስጥ ቀዳሚዋ ሆናለች ብለዋል።
የዕድገት ምጣኔን በተመለከተም ኢትዮጵያ በ9.2 በመቶ የዕድገት ግስጋሴ ላይ መሆኗን ጠቅሰው፣ ይህም አገሪቱ የጀመረችው የማክሮ-ኢኮኖሚ ማሻሻያ ውጤት መሆኑን አመልክተዋል።
የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) በ2026 ባወጣው ሪፖርት፣ ኢትዮጵያ መንግሥት አቅዶት ከነበረው 9.2 በመቶ በ0.1 ከፍ ያለ የ9.3 በመቶ ዕድገት እንደምታስመዘግብ መተንበዩን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በደስታ ገልጸዋል።
ይህ የኢኮኖሚ ዕድገት ግስጋሴ ኢትዮጵያ በአኅጉራዊና በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን የኢኮኖሚ ተፅዕኖ ፈጣሪነት የሚያረጋግጥ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው አጽንኦት ሰጥተውበታል።


አስተያየትዎን ይተው