ከይር ቮክስ አፍሪካ

ከይር ቮክስ አፍሪካ

ዜና አለም አቀፍ

ቡርኪና ፋሶ ከአስር ቀናት በፊት በቁጥጥር ስር አውላቸው የነበረ 11 የናይጄሪያ አየር ኃይል አባላትን ለቀቀች።

on | 2025-12-18 15:41:06

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin


ቡርኪና ፋሶ ከአስር ቀናት በፊት በቁጥጥር ስር አውላቸው የነበረ 11 የናይጄሪያ አየር ኃይል አባላትን ለቀቀች።

 ቡርኪና ፋሶ የናይጄሪያ የአየር ኃይል አባላትን በቁጥጥር ስር ያዋላቸው ንብረትነቱ የናይጄሪያ አየር ኃይል የሆነ አውሮፕላን ድንገት በግዛቷ ማረፉን ተከትሎ ነበር። 

ወታደሮቹ የተለቀቁት  በኢብራሂም ታራኦሬ የሚመራው የቡርኪና ፋሶ ወታደራዊ አስተዳደር ከናይጄሪያ ልዑካን ጋር ከተደራደረ በኋላ መሆኑን ገልጿል። 

በድንገት ቡርኪና ፋሶ ውስጥ ማረፉ የተገለጸው አውሮፕላን ሁለት አብራሪዎች እና ዘጠኝ ተሳፋሪዎች ይዞ እንደነበር የአሶሽየትድ ፕረስ ዘገባ ያመለከተው። 

የናይጄሪያ አየር ኃይል ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ ድንገት ምዕራባዊ ቡርኪና ፋሶ ውስጥ ለማረፍ የተገደደው አውሮፕላን ለጥገና ወደ ፖርቹጋል ሲያቀና ነበር ብሏል። 

ድርድሩን ተከትሎ ናይጄሪያ እና ቡርኪናፋሶ መደበኛ ምክክር ለማድረግ እና የሁለትዮሽ ትብብር እና ቀጠናዊ ውህደትን ለማጠናከር መስማማታቸውን የናይጄሪያ ተደራዳሪ ቡድን ቃል አቃባይ አልቃሲም አብዱልቃድር ተናግረዋል። 

አውሮፕላኑን በድንገት ለማሳረፍ ያስገደደው ኹነት   የተከሰተው በሳሄል ግዛቶች እና በናይጄሪያ መካከል ያለው ግንኙነት በተቋረጠበት ወቅት መሆኑ ነው የተገለጸው።

ናይጄሪያ ከሁለት ሳምንት በፊት  ቤኒን ውስጥ የተፈጸመውን የአጭር ጊዜ መፈንቅለ መንግስት ለመቀልበስ በሚረዱ የጣልቃ ገብነት ጥረቶች ላይ የተሳተፈች  ሲሆን የአየር ሃይሏም በመፈንቅለ መንግስቱ ፈጻሚዎች ላይ ያነጣጠረ የአየር ድብደባ ማድረጉን ዘገባው አመልክቷል።

ናይጄሪያ የምዕራብ አፍሪቃ የኤኮኖሚ ማህበረሰብ ኤኮዋስን ከመሰረቱ አስራ አምስቱ ሃገራት አንዷ ስትሆን ቡርኪና ፋሶ ደግሞ ልክ እንደ ማሊ እና ኒጀር ሁሉ ክልላዊ ጥምረቱን ለቃ በመውጣት ሌላ የሳህል ህብረት የተባለ እና በወታደራዊ አስተዳደር ስር ያሉ ሃገራቱ የጋራ ጥምረት ፈጥረዋል።

ፈልግ

አስተያየትዎን ይተው