on | 2025-12-18 15:27:11
Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin
መቀመጫውን በደቡብ ምዕራባዊቷ የጀርመን ከተማ ካርልስሩኸ ያደረገው ዐቃቤ ሕግ ተጠርጣሪዎቹን በሀገር ውስጥ የአሸባሪ ድርጅት አባልነት፣ የግድያ ሙከራ፣ ግድያ ለመፈጸም በማሴር እና ከባድ የአካል ጉዳትን ጨምሮ በተለያዩ የወንጀል ክሶች መመስረቱን አስታውቋል።
በርከት ያለ ክስ ከቀረበባቸው እነዚሁ የቀኝ ጽንፈኛ ቡድን አባላት ውስጥ አንዳንዶቹ በአስራዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ እንደሚገኙ አቃቤ ሕግ ገልጿል።
የጀርመን ፖሊስ የቀኝ አክራሪ ጽንፈኛ ቡድን አባላትን በቁጥጥር ስር ለማዋል ካለፈው ዓመት የግንቦት ወር ጀምሮ ዘመቻ መክፈቱን የጀርመን ዜና አገልግሎት ዘገባ ያመለክታል።
ከዚያ ጊዜ አንስቶ የሀገሪቱ ፖሊስ በተለያዩ ክልሎች የሚንቀሳቀሰው እና ራሱን «የመጨረሻው የመከላከያ ማዕበል » ብሎ የሚጠራው ይኸው የቀኝ አክራሪ ጽንፈኛ ቡድን ላይ ያነጣጠረ ዘመቻ ሲያካሄድ ቆይቷል።
የሀገሪቱ ዐቃቤ ሕግ እንደሚለው ቡድኑ ራሱን እንደ «የጀርመን ሀገር አዳኝ» ሲቆጥር ፤ ዓላማውም የሀገሪቱን ዴሞክራሲያዊ ሥረዓት በኃይል ማፍረስ እና በዋነኛነት ደግሞ በስደተኞች እና የፖለቲካ ተቃዋሚዎች ላይ ጥቃት ማድረስ ነው ።
ፖሊስ ባለፈው የግንቦት ወር በከፈተው ዘመቻ በቁጥጥር ስር ያዋላቸው ሁሉም ከ14 እስከ 21 ዓመት የሆኑ ታዳጊዎች እና ወጣቶች ሲሆኑ እስከ አሁንም ድረስ በእስር ላይ መቆየታቸውን ዘገባው አመልክቷል።
በወላይታ ብሔር ዘንድ ልዩ ቦታ የሚሰጠው "ጊፋታ”
በቶኪዮ የወርቅ መርገም አልሰበር ያላት ኢትዮጲያ