on | 2025-12-18 13:26:04 on2026-01-15 08:05:49
Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin
አዲስ አበባ | ኪይር ዜና
በፍሊፐር ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት ላንቺያ ግቢ የሚገኙ የተማሪዎች ወላጆች የከተማው ባለስልጣናት
ትምህርት ቤቱ ግቢውን ለቆ እንዲወጣ ካዘዙ በኋላ እየጨመረ የመጣውን ስጋት እየገለጹ ነው። የወላጆች ጭንቀት የጨመረው የኦሮሚያ
ፖሊስ ኮሚሽን ዋና መሥሪያ ቤትን ለማስፋፋት ሲባል ት/ቤቱ ቦታውን እንዲለቅ ትእዛዝ ከተሰጠው በኋላ ነው።
ውሳኔው ከአንደኛ ክፍል እስከ አምስኛ ክፍል ያሉ ወደ 800 የሚጠጉ ተማሪዎችን ስጋት ውስጥ
አስገብቷል። ከአስር አመት በላይ ሲሰራ የቆየው የላንቺያ ካምፓስ በአዲስ አበባ የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ባፀደቀው የመሬት
ዝውውር ተጎጂ ከሆኑ በርካታ ባለይዞታዎች መካከል አንዱ ነው።
በቅርቡ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ባለ 13 ፎቅ ዋና መሥሪያ ቤት በ700 ሚሊዮን ብር በላይ
በሆነ ወጪ ካስመረቀ በኋላ ቦታው ለመኪና ማቆሚያ እንደሚያስፈልገው ኮሚሽኑ ለከተማው መስተዳድር መጠየቁ ይታወሳል። የከተማ አስተዳደሩ
ለኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ተጨማሪ 6,822 ካሬ ሜትር ለመኪና ማቆሚያ ማስፋፊያከሰጠ በኋላ ለባለይዞታዎች ካሳ የመክፈል ሃላፊነትን
በኮሚሽኑ እንደፈፀም አዟል።
ከሁለት ሳምንታት በፊት ትምህርት ቤቱ ለወላጆች ትዕዛዙን ያሳወቀ ሲሆን ትምህርቱ እስከ የዘንድሮው
የትምህርት ዘመን መጨረሻ ድረስ እንደሚቀጥል አረጋግጦላቸዋል። ሆኖም ትምህርት ቤቱ እስካሁን አማራጭ ቦታ እንዳላገኘ አምኖ በመቀበል
በተለይም በከተማው ውስጥ ያሉ አብዛኛዎቹ ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች በሙሉ አቅም እየሰሩ በመሆናቸው በቤተሰቦች ዘንድ ስጋት ፈጥሯል።
የፍሊፐር አስተዳደር ተስማሚ የሆነ የማዛወሪያ ቦታ ለማግኘት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ቢናገሩም ወላጆች ውሳኔው በተማሪዎች የትምህርት ቀጣይነት እና ደህንነት ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ በመፍራት ስጋት ውስጥ ወድቀዋል።
ምንጭ፡- አዲስ ፎርቹን
በወላይታ ብሔር ዘንድ ልዩ ቦታ የሚሰጠው "ጊፋታ”
በቶኪዮ የወርቅ መርገም አልሰበር ያላት ኢትዮጲያ