ከይር ቮክስ አፍሪካ

ዜና የሀገር ውስጥ

የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ለሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት አዲስ_አበባ ገብተዋል::

on | 2025-12-16 16:06:24

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin


የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ለሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት አዲስ_አበባ ገብተዋል::

የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ታሪካዊ የተባለለትን የሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት በኢትዮጵያ ለማከናወን አዲስ አበባ ገቡ። 

ናሬንድራ ሞዲ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) እና ሌሎች ሚኒስትሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጠ/ሚ ናሬንድራ በቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር በኢንቨስትመንት እና በሳይበር ደህንነት ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩ ተጠቁሟል።

በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኒል ኩማር ራይ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ ትኩረት በሚሰጥባቸው የሁለትዮሽ ግንኙነት ጉዳዮች ማለትም በኢንቨስትመንት፣ በግብርና፣ በማዕድን ልማት፣ በዲጂታል መሠረተ ልማት እና በሳይበር ደህንነት ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር ሰፊ ውይይት እንደሚያደርጉ ቀደም ሲል ተናግረዋል።

ነገ በሚካሄደው በኢፌዴሪ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የጋራ ስብሰባ ላይም የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቋል። 

በተጨማሪም ቁጥራቸው 2,500 የሚጠጋውን በኢትዮጵያ የሚኖሩ ህንዳውያን ማኅበረሰብን እንደሚያገኙ የተገለፀ ሲሆን፤ ለእርሳቸው ክብር በተዘጋጁ ልዩ ልዩ የባህልና የእንኳን ደህና መጡ ዝግጅቶች ላይ ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ፈልግ

አስተያየትዎን ይተው