ከይር ቮክስ አፍሪካ

ዜና የሀገር ውስጥ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በሔራዊ ባንክ ያስቀመጠውን ዘቅተኛ የተከፈለ ካፒታል ከቀነንደቡ በፊት ማሟላቱ ተገለፀ

on | 2025-12-12 19:48:17

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin


ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በሔራዊ ባንክ ያስቀመጠውን ዘቅተኛ የተከፈለ ካፒታል ከቀነንደቡ በፊት ማሟላቱ ተገለፀ

አዲስ አበባ:- ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በሔራዊ ባንክ ያስቀመጠውን ዘቅተኛ የተከፈለ ካፒታል ከቀነ ገደቡ በፊት ማሟላቱ ተገለፀ።

 ባንኩ የተከፈለ ካፒታሉን በማሳደግ 5 ቢሊዮን ብር ማድረስ መቻሉን የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ ገልጸዋል።

ይህ አፈጻጸም ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር የ102 በመቶ እድገት ማሳየቱን ገልጸዋል።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በ2024/2025 በጀት አመት ከ5.5 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱ የተገለጸ ሲሆን ዘንድሮ የተመዘገበው የባንኩ የባንክ ገቢ ባለፈው አመት ከተመዘገበው ገቢ ሲነጻጸር የ37 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ተናግረዋል።

በበደጀት አመቱ ባንኩ 7.53 ቢሊዮን ብር ተቀማጭ ገንዘብ መሰብሰብ የቻለ ሲሆን ይህም ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር የ41 በመቶ ብልጫ በማሳየት የባንኩን አጠቃላይ ተቀማጭ የገንዘብ መጠን ወደ 25.75 ቢሊዮን ማዳረስ መቻሉን ተናግረዋል።

በተጠናቀቀው በጀት አመት ከአለም አቀፍ የማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች መቀዛቀዝ ጋር ተዳምሮ በሀገራችንም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ የኢኮኖሚ ሁኔታው አለመረጋጋት ያሳየ ቢሆንም ባንኩ በበጀት አመቱ ከታክስ ከመጠባበቂያ እና ሌሎች ተቀናሾች በፊት ከ1.17 ቢሊዮን ብር በላይ ማትረፍ ችሏል።

ፈልግ

አስተያየትዎን ይተው