on | 2025-12-12 14:58:46
Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin
ከ450 በላይ የሚሆኑ የሀገር ውስጥ እና ከአስር በላይ ሀገራት የተወጣጡ ልዩ ልዩ አምራቾች እና አገልግሎት ሰጪዎች የሚሳተፉበት የገና ኤክስፖ ከታህሳስ 4 እስከ ገና ዋዜማ ታህሳስ 28 ድረስ ይካሄዳል ተብሏል።
ኤክስፖው በዳሶማ ትሬዲንግ ሃላፊነቱ የተ/ የግ/ ማህበር አዘጋጅነት በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ይከፈታል ተብሏል።
በዘንድሮ ኤክስፖ ላይ በሀገሪቱ የሚገኙ የፋይናንስ ተቋማት፣ የሪል ስቴት አልሚዎች፣ የተሽከርካሪ መኪና አስመጪዎች፣ የሸማች ማህበራት፣ የሸቀጣ ሸቀጥ እና የእለት ፍጆታ አቅራቢዎች፣ የአዋቂ እና የህፃናት አልባሳት እንዲሁም የቤት ውስጥ እቃዎችና የፈርኒቸር ውጤቶች የሚያቀርቡ ተቋማት የሚገኙ ሲሆን ለህብረተሰቡ በአነስተኛ ዋጋ ምርቶችን የሚያቀርቡ ቀጥተኛ አምራቾች፣ የንግድ ወኪሎች፣ አገልግሎት ሰጪዎችና ሌሎች ተቋማትም የሚሳተፉ ይሆናል።
የተጋነነውን የዋጋ ንረት ለማስቀረት ሸማቹ ምርቱን ቀጥታ ከአምራች እና አስመጪዎች ላይ የሚገበያይበትን ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ሲሆን የህፃናት ጌም ዞኖች እንዲሁም ጣፍጭ ምግቦችና መጠጦች በበቂ ሁኔታ ይቀርባሉ።
በየኢንተርቴይመንት በኩል ታዋቂ ድምፃዊያን በየቀኑ የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ከመድረክ ላይ ያቀርባሉ።
በኤክስፖ ላይ ማህበራዊ ኃላፊነትን ለመወጣት ለበርካታ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ነፃ ቦታ በመፍቀድ ማህበራቸውን እንዲያስተዋውቁ እድል የሚሰጥ ከመሆኑም በላይ የበዓሉም ዕለት እጅ ያጠራቸውን ወገኖች በዓልን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተደስተው እንዲውሉ ዳሶማ ትሬዲንግ ድጋፍ ያደርጋል።
በተከታታይ 25 ቀናት በሚደረገው ኤክስፖ ላይ በየቀኑ የተለያዩ አጓጊ ሸልማቶች የሚኖሩ ሲሆን ታህሳስ 28 በሚኖረው የመዝጊያ ስነስርዓት ላይ የመኪና ሽልማት በመስጠት የኤክስፖው ማጠቃለያ ይሆናል።
በተጨማሪም በኤክስፖው ማጠናቀቂያ ላይ ሸማቾችን የመኪና እድለኛ የሚደርገውንም አሰራር ከብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ጋር በዕጣ አወጣጡ ዙሪያ እየተሰራ ይገኛል።